1
የሐካልያ ልጅ የነህምያ ቃል። በሀያኛው ዓመት በካሴሉ ወር እንዲህ ሆነ፤
2
እኔ በሱሳ ግንብ ሳለሁ፥ ከወንድሞቼ አንዱ አናኒ ከእርሱም ጋር ሌሎች ሰዎች ከይሁዳ መጡ፤ እኔም የዳኑትን ከምርኮ የተረፉትን የአይሁድን ነገር የኢየሩሳሌምንም ነገር ጠየቅኋቸው።
3
እነርሱም። በዚያ ስፍራ ያሉት ከምርኮ የተረፉት ቅሬታዎች በታላቅ መከራና ስድብ አሉ፤ የኢየሩሳሌምም ቅጥር ፈርሶአል፥ በሮችዋም በእሳት ተቃጥለዋል አሉኝ።
4
ይህንም ቃል በሰማሁ ጊዜ ተቀምጬ አለቀስሁ፥ አያሌ ቀንም አዝን ነበር፤ በሰማይም አምላክ ፊት እጾምና እጸልይ ነበር፥
5
እንዲህም አልሁ። አቤቱ የሰማይ አምላክ ሆይ፥ ለሚወድዱህና ትእዛዝህን ለሚያደርጉ ቃል ኪዳንንና ምሕረትን የምትጠብቅ፥ ታላቅና የተፈራህ አምላክ ሆይ፥
6
እኔ ባሪያህ ዛሬ በፊትህ ስለ ባሪያዎችህ ስለ እስራኤል ልጆች ሌሊትና ቀን የምጸልየውን ጸሎት ትሰማ ዘንድ ጆሮህ ያድምጥ፥ ዓይኖችህም ይከፈቱ፤ በአንተ ላይም ያደረግነውን የእስራኤልን ልጆች ኃጢአት እናዘዝልሃለሁ፤ እኔና የአባቴም ቤት በድለናል።
7
እኛም በአንተ ላይ እጅግ ክፉ ሠርተናል፤ ለባሪያህም ለሙሴ ያዘዝኸውን ትእዛዝና ሥርዓት ሕግም አልጠበቅንም።
8-9
አሁንም ብትተላለፉ በአሕዛብ መካከል እበትናችኋለሁ፤ ወደ እኔ ብትመለሱ ግን ትእዛዜንም ብትጠብቁ ብታደርጓትም፥ ከእናንተ ሰዎች እስከ ሰማይ ዳርቻ ድረስ ምንም ቢበተኑ ከዚያ እሰበስባቸዋለሁ፥ ስሜም ይኖርበት ዘንድ ወደ መረጥሁት ስፍራ አመጣቸዋለሁ ብለህ ለባሪያህ ለሙሴ ያዘዝኸውን ቃል እባክህ አስብ።
10
እነዚህም በታላቅ ኃይልህና በብርቱ እጅህ የተቤዠሃቸው ባሪያዎችህና ሕዝብህ ናቸው።
11
ጌታ ሆይ፥ ጆሮህ የባሪያህን ጸሎት፥ ስምህንም ይፈሩ ዘንድ የሚወድዱትን፥ የባሪያዎችህን ጸሎት ያድምጥ፤ ዛሬም ለባሪያህ አከናውንለት፥ በዚህም ሰው ፊት ምሕረትን ስጠው። እኔም ለንጉሡ ጠጅ አሳላፊው ነበርሁ።

1
The words of Nehemiah the son of Hacaliah. Now it happened in the month Chislev, in the twentieth year, as I was in Shushan the palace,
2
that Hanani, one of my brothers, came, he and certain men out of Judah; and I asked them concerning the Jews who had escaped, who were left of the captivity, and concerning Jerusalem.
3
They said to me, The remnant who are left of the captivity there in the province are in great affliction and reproach: the wall of Jerusalem also is broken down, and the gates of it are burned with fire.
4
It happened, when I heard these words, that I sat down and wept, and mourned certain days; and I fasted and prayed before the God of heaven,
5
and said, I beg you, Yahweh, the God of heaven, the great and awesome God, who keeps covenant and loving kindness with those who love him and keep his commandments:
6
Let your ear now be attentive, and your eyes open, that you may listen to the prayer of your servant, which I pray before you at this time, day and night, for the children of Israel your servants while I confess the sins of the children of Israel, which we have sinned against you. Yes, I and my father''s house have sinned:
7
we have dealt very corruptly against you, and have not kept the commandments, nor the statutes, nor the ordinances, which you commanded your servant Moses.
8
Remember, I beg you, the word that you commanded your servant Moses, saying, If you trespass, I will scatter you abroad among the peoples:
9
but if you return to me, and keep my commandments and do them, though your outcasts were in the uttermost part of the heavens, yet will I gather them from there, and will bring them to the place that I have chosen, to cause my name to dwell there.
10
Now these are your servants and your people, whom you have redeemed by your great power, and by your strong hand.
11
Lord, I beg you, let now your ear be attentive to the prayer of your servant, and to the prayer of your servants, who delight to fear your name; and please prosper your servant this day, and grant him mercy in the sight of this man. Now I was cup bearer to the king.