1
ዖፅ በሚባል አገር ስሙ ኢዮብ የተባለ አንድ ሰው ነበረ፤ ያም ሰው ፍጹምና ቅን፥ እግዚአብሔርንም የሚፈራ፥ ከክፋትም የራቀ ነበረ።
2
ሰባትም ወንዶች ሦስትም ሴቶች ልጆች ተወልደውለት ነበር።
3
ሀብቱም ሰባት ሺህ በጎች፥ ሦስት ሺህም ግመሎች፥ አምስት መቶም ጥማድ በሬ፥ አምስት መቶም እንስት አህዮች ነበረ፥ እጅግ ብዙም ባሪያዎች ነበሩት፤ ያም ሰው በምሥራቅ ካሉ ሰዎች ሁሉ ይልቅ ታላቅ ነበረ።
4
ወንዶች ልጆቹም ሄደው በየተራ በያንዳንዳቸው ቤት ግብዣ ያደርጉ ነበር፤ ሦስቱ እኅቶቻቸውም ከእነርሱ ጋር ይበሉና ይጠጡ ዘንድ እነርሱ ልከው ይጠሩአቸው ነበር።
5
የግብዣውም ቀኖች ባለፉ ጊዜ ኢዮብ። ምናልባት ልጆቼ በድለው፥ እግዚአብሔርንም በልባቸው ሰድበው ይሆናል ብሎ ይልክና ይቀድሳቸው ነበር፤ ኢዮብም ማልዶ ተነሣ፥ እንደ ቍጥራቸውም ሁሉ የሚቃጠል መሥዋዕት አቀረበ። እንዲሁ ኢዮብ ሁልጊዜ ያደርግ ነበር።
6
ከዕለታት አንድ ቀን እንዲህ ሆነ፤ የአምላክ ልጆች በእግዚአብሔር ፊት ለመቆም መጡ፥ ሰይጣንም ደግሞ በመካከላቸው መጣ።
7
እግዚአብሔርም ሰይጣንን። ከወዴት መጣህ? አለው። ሰይጣንም። ምድርን ሁሉ ዞርሁአት፥ በእርስዋም ተመላለስሁ ብሎ ለእግዚአብሔር መለሰ።
8
እግዚአብሔርም ሰይጣንን። በውኑ ባሪያዬን ኢዮብን ተመለከትኸውን? በምድር ላይ እንደ እርሱ ፍጹምና ቅን፥ እግዚአብሔርንም የሚፈራ፥ ከክፋትም የራቀ ሰው የለም አለው።
9
ሰይጣንም ለእግዚአብሔር እንዲህ ብሎ መለሰለት። በውኑ ኢዮብ እግዚአብሔርን የሚፈራ በከንቱ ነውን?
10
እርሱንና ቤቱን በዙሪያውም ያሉትን ሁሉ አላጠርህለትምን? የእጁን ሥራ ባርከህለታል፥ ከብቱም በምድር ላይ በዝቶአል።
11
ነገር ግን እጅህን ዘርግተህ ያለውን ሁሉ ዳብስ፤ በእውነት በፊትህ ይሰድብሃል።
12
እግዚአብሔርም ሰይጣንን። እነሆ ለእርሱ ያለው ሁሉ በእጅህ ነው፥ ነገር ግን በእርሱ ላይ እጅህን አትዘርጋ አለው። ሰይጣንም ከእግዚአብሔር ፊት ወጣ።
13
አንድ ቀንም እንዲህ ሆነ፤ የኢዮብ ወንዶችና ሴቶች ልጆች በታላቅ ወንድማቸው ቤት ይበሉና የወይን ጠጅ ይጠጡ ነበር።
14
መልክተኛም ወደ ኢዮብ መጥቶ። በሬዎች እርሻ ያርሱ፥ በአጠገባቸውም አህዮች ይሰማሩ ነበር፤
15
የሳባም ሰዎች አደጋ ጣሉ፥ ወሰዱአቸውም፥ ብላቴኖቹንም በሰይፍ ስለት ገደሉ፤ እኔም እነግርህ ዘንድ ብቻዬን አመለጥሁ አለው።
16
እርሱም ገና ሲናገር ሌላ መጥቶ። የእግዚአብሔር እሳት ከሰማይ ወደቀች፥ በጎቹንም አቃጠለች፥ ጠባቂዎችንም በላች፤ እኔም እነግርህ ዘንድ ብቻዬን አመለጥሁ አለው።
17
እርሱም ገና ሲናገር ሌላ መጥቶ። ከለዳውያን በሦስት ረድፍ ተከፍለው በግመሎች ላይ አደጋ ጣሉ፥ ወሰዱአቸውም፥ ብላቴኖቹንም በሰይፍ ስለት ገደሉ፤ እኔም እነግርህ ዘንድ ብቻዬን አመለጥሁ አለው።
18
እርሱም ገና ሲናገር ሌላ መጥቶ። ወንዶችና ሴቶች ልጆችህ በታላቅ ወንድማቸው ቤት ይበሉና የወይን ጠጅ ይጠጡ ነበር፤
19
እነሆም፥ ዐውሎ ነፋስ ከምድረ በዳ መጥቶ የቤቱን አራቱን ማዕዘን መታው፥ በብላቴኖቹም ላይ ወደቀ፥ ሞቱም፤ እኔም እነግርህ ዘንድ ብቻዬን አመለጥሁ አለው።
20
ኢዮብም ተነሣ መጐናጸፊያውንም ቀደደ፥ ራሱንም ተላጨ፥ በምድርም ላይ ተደፍቶ ሰገደ፤
21
እንዲህም አለ። ራቁቴን ከእናቴ ማኅፀን ወጥቻለሁ፥ ራቁቴንም ወደዚያ እመለሳለሁ፤ እግዚአብሔር ሰጠ፥ እግዚአብሔርም ነሣ፤ የእግዚአብሔር ስም የተባረከ ይሁን።
22
በዚህ ሁሉ ኢዮብ አልበደለም፥ ለእግዚአብሔርም ስንፍናን አልሰጠም።

1
There was a man in the land of Uz whose name was Job. He was without sin and upright, fearing God and keeping himself far from evil.
2
And he had seven sons and three daughters.
3
And of cattle he had seven thousand sheep and goats, and three thousand camels, and a thousand oxen, and five hundred she-asses, and a very great number of servants. And the man was greater than any of the sons of the east.
4
His sons regularly went to one another's houses, and every one on his day gave a feast: and at these times they sent for their three sisters to take part in their feasts with them.
5
And at the end of their days of feasting, Job sent and made them clean, getting up early in the morning and offering burned offerings for them all. For, Job said, It may be that my sons have done wrong and said evil of God in their hearts. And Job did this whenever the feasts came round.
6
And there was a day when the sons of the gods came together before the Lord, and the Satan came with them.
7
And the Lord said to the Satan, Where do you come from? And the Satan said in answer, From wandering this way and that on the earth, and walking about on it.
8
And the Lord said to the Satan, Have you taken note of my servant Job, for there is no one like him on the earth, a man without sin and upright, fearing God and keeping himself far from evil?
9
And the Satan said in answer to the Lord, Is it for nothing that Job is a god-fearing man?
10
Have you yourself not put a wall round him and his house and all he has on every side, blessing the work of his hands, and increasing his cattle in the land?
11
But now, put out your hand against all he has, and he will be cursing you to your face.
12
And the Lord said to the Satan, See, I give all he has into your hands, only do not put a finger on the man himself. And the Satan went out from before the Lord.
13
And there was a day when his sons and daughters were feasting in the house of their oldest brother,
14
And a man came to Job, and said, The oxen were ploughing, and the asses were taking their food by their side:
15
And the men of Sheba came against them and took them away, putting the young men to the sword, and I was the only one who got away safe to give you the news.
16
And this one was still talking when another came, and said, The fire of God came down from heaven, burning up the sheep and the goats and the young men completely, and I was the only one who got away safe to give you the news.
17
And this one was still talking when another came, and said, The Chaldaeans made themselves into three bands, and came down on the camels and took them away, putting the young men to the sword, and I was the only one who got away safe to give you the news.
18
And this one was still talking when another came, and said, Your sons and your daughters were feasting together in their oldest brother's house,
19
When a great wind came rushing from the waste land against the four sides of the house, and it came down on the young men, and they are dead; and I was the only one who got away safe to give you the news.
20
Then Job got up, and after parting his clothing and cutting off his hair, he went down on his face to the earth, and gave worship, and said,
21
With nothing I came out of my mother's body, and with nothing I will go back there; the Lord gave and the Lord has taken away; let the Lord's name be praised.
22
In all this Job did no sin, and did not say that God's acts were foolish.