1
ስለዚህም ልቤ ተንቀጠቀጠ፥ ከስፍራውም ተንቀሳቀሰ።
2
የድምፁን መትመም ስሙ፥ ከአፉም የሚወጣውን ጕርምርምታ አድምጡ።
3
እርሱን ወደ ሰማያት ሁሉ ታች፥ ብርሃኑንም ወደ ምድር ዳርቻ ይሰድዳል።
4
በስተ ኋላው ድምፅ ይጮኻል፤ በግርማውም ድምፅ ያንጐደጕዳል፤ ድምፁም በተሰማ ጊዜ መብረቁን አይከለክልም።
5
እግዚአብሔር በድምፁ ድንቅኛ ያንጐደጕዳል፤ እኛም የማናስተውለውን ታላቅ ነገር ያደርጋል።
6
በረዶውንና ውሽንፍሩን ብርቱንም ዝናብ። በምድር ላይ ውደቁ ይላል።
7
ሰው ሁሉ ሥራውን ያውቅ ዘንድ የሰውን ሁሉ እጅ ያትማል።
8
አውሬዎቹም ወደ ጫካው ይገባሉ፥ በዋሾቻቸውም ይቀመጣሉ።
9
ከተሰወረ ማደሪያውም ዐውሎ ነፋስ፥ ከሰሜንም ብርድ ይወጣል።
10
ከእግዚአብሔር እስትንፋስ ውርጭ ተሰጥቶአል፤ የውኆችም ስፋት ይጠብባል።
11
የውኃውንም ሙላት በደመና ላይ ይጭናል፤ የብርሃኑንም ደመና ይበታትናል፤
12-13
ለተግሣጽ ወይም ለምድሩ ወይም ለምሕረት ቢሆን፥ ሰው በሚኖርበት ዓለም ላይ ያዘዘውን ሁሉ ያደርግ ዘንድ ፈቃዱ ወደ መራችው ይዞራል።
14
ኢዮብ ሆይ፥ ይህን ስማ፤ ቁም፥ የእግዚአብሔርንም ተአምራት አስብ።
15
በውኑ እግዚአብሔር እንዴት እንደሚያዝዛቸው፥ የደመናውንም ብርሃን እንዴት እንደሚያበራ አውቀሃልን?
16
ወይስ የደመናውን ሚዛን፥ ወይስ በእውቀት ፍጹም የሆነውን ተአምራት አውቀሃልን?
17
በደቡብ ነፋስ ምድር ጸጥ ባለች ጊዜ፥ ልብስህ የሞቀች አንተ ሆይ፥
18
እንደ ቀለጠ መስተዋት ብርቱ የሆኑትን ሰማያት ከእርሱ ጋር ልትዘረጋ ትችላለህን?
19
እኛ ከጨለማ የተነሣ በሥርዓት መናገር አንችልምና የምንለውን አስታውቀን።
20
ማንም በእርሱ ላይ ቢናገር ፈጽሞ ይዋጣልና እኔ እናገር ዘንድ ብወድድ ሰው ይነግረዋልን?
21
አሁንም ነፋስ አልፎ ካጠራቸው በኋላ፥ ሰው በሰማያት የሚበራውን ብርሃን ሊመለከት አይችልም።
22
ከሰሜን ወርቅ የሚመስል ጌጠኛ ብርሃን ይወጣል፤ በእግዚአብሔር ዘንድ የሚያስፈራ ግርማ አለ።
23
ሁሉን የሚችል አምላክን እናገኝ ዘንድ አንችልም፤ በኃይል ታላቅ ነው፤ በፍርድና በጽድቅም አያስጨንቅም።
24
ስለዚህ ሰዎች ይፈሩታል፤ በልባቸውም ጠቢባን የሆኑትን ሁሉ አይመለከትም።

1
"Yes, at this my heart trembles, and is moved out of its place.
2
Hear, oh, hear the noise of his voice, the sound that goes out of his mouth.
3
He sends it forth under the whole sky, and his lightning to the ends of the earth.
4
After it a voice roars. He thunders with the voice of his majesty. He doesn''t hold back anything when his voice is heard.
5
God thunders marvelously with his voice. He does great things, which we can''t comprehend.
6
For he says to the snow, ''Fall on the earth;'' likewise to the shower of rain, and to the showers of his mighty rain.
7
He seals up the hand of every man, that all men whom he has made may know it.
8
Then the animals take cover, and remain in their dens.
9
Out of its chamber comes the storm, and cold out of the north.
10
By the breath of God, ice is given, and the breadth of the waters is frozen.
11
Yes, he loads the thick cloud with moisture. He spreads abroad the cloud of his lightning.
12
It is turned round about by his guidance, that they may do whatever he commands them on the surface of the habitable world,
13
Whether it is for correction, or for his land, or for loving kindness, that he causes it to come.
14
"Listen to this, Job. Stand still, and consider the wondrous works of God.
15
Do you know how God controls them, and causes the lightning of his cloud to shine?
16
Do you know the workings of the clouds, the wondrous works of him who is perfect in knowledge?
17
You whose clothing is warm, when the earth is still by reason of the south wind?
18
Can you, with him, spread out the sky, which is strong as a cast metal mirror?
19
Teach us what we shall tell him, for we can''t make our case by reason of darkness.
20
Shall it be told him that I would speak? Or should a man wish that he were swallowed up?
21
Now men don''t see the light which is bright in the skies, but the wind passes, and clears them.
22
Out of the north comes golden splendor. With God is awesome majesty.
23
We can''t reach the Almighty. He is exalted in power. In justice and great righteousness, he will not oppress.
24
Therefore men revere him. He doesn''t regard any who are wise of heart."