1
ነፍሴ ሆይ፥ እግዚአብሔርን ባርኪ፤ አቤቱ አምላኬ ሆይ፥ አንተ እጅግ ታላቅ ነህ፤ ክብርንና ግርማን ለበስህ።
2
ብርሃንን እንደ ልብስ ለበስህ፤ ሰማይንም እንደ መጋረጃ ዘረጋህ፤
3
እልፍኙን በውኃ የሚሠራ፥ ሰረገላውን ደመና የሚያደርግ፥ በነፋስ ክንፍም የሚሄድ፥
4
መላእክቱን መንፈስ የሚያደርግ፥ አገልጋዮቹንም የእሳት ነበልባል።
5
ለዘላለም እንዳትናወጥ ምድርን በመሠረትዋ ላይ መሠረታት።
6
በጥልቅ እንደ ልብስ ከደንሃት፥ በተራሮችም ላይ ውኆች ይቆማሉ።
7
ከዘለፋህም ይሸሻሉ፥ ከነጐድጓድህም ድምፅ ይደነግጣሉ፤
8
ወደ ተራሮች ይወጣሉ፥ ወደ ቈላዎች ወዳዘጋጀህላቸው ስፍራ ይወርዳሉ፤
9
እንዳያልፉትም ድንበር አደረግህላቸው ምድርን ይከድኑ ዘንድ እንዳይመለሱ።
10
ምንጮችን ወደ ቈላዎች ይልካል፤ በተራሮች መካከል ውኆች ያልፋሉ፤
11
የዱር አራዊትን ሁሉ ያጠጣሉ፥ የበረሃ አህያዎችም ጥማታቸውን ይረካሉ።
12
የሰማይም ወፎች በእነርሱ ዘንድ ያድራሉ፥ በድንጋዩ ስንጥቅ መካከልም ይጮኻሉ።
13
ተራሮችን ከላይ የሚያጠጣቸው፤ ከሥራህ ፍሬ ምድር ትጠግባለች።
14
እንጀራን ከምድር ያወጣ ዘንድ ለምለሙን ለሰው ልጆች ጥቅም፥ ሣርንም ለእንስሳ ያበቅላል።
15
ወይን የሰውን ልብ ደስ ያሰኛል፥ ዘይትም ፊትን ያበራል፥ እህልም የሰውን ጕልበት ያጠነክራል።
16
የእግዚአብሔር ዛፎች እርሱም የተከላቸው የሊባኖስ ዝግባዎች ይጠግባሉ።
17
በዚያም ወፎች ይዋለዳሉ፥ የሽመላ ቤትም የእነርሱ ጎረቤት ነው።
18
ረጃጅም ተራራዎች ለዋላዎች፥ ድንጋዮችም ለእሽኮኮች መሸሻ ናቸው።
19
ጨረቃን ለጊዜዎች አደረገ፤ ፀሐይም መግቢያውን ያውቃል።
20
ጨለማ ታደርጋለህ ሌሊትም ይሆናል፤ በእርሱም የዱር አራዊት ሁሉ ይወጡበታል።
21
የአንበሳ ግልገሎች ለመንጠቅ ይጮኻሉ፥ ከእግዚአብሔርም ምግባቸውን ይሻሉ።
22
ፀሐይ ስትወጣ ይሰበሰባሉ በየዋሻቸውም ይተኛሉ።
23
ሰው ወደ ተግባሩ፥ እስኪመሽም ድረስ ወደ ሥራው ይወጣል።
24
አቤቱ፥ ሥራህ እጅግ ብዙ ነው፤ ሁሉን በጥበብ አደረግህ፥ ምድርም ከፍጥረትህ ተሞላች።
25
ይህች ባሕር ታላቅና ሰፊ ናት፤ በዚያ ስፍራ ቍጥር የሌለው ተንቀሳቃሽ፥ ታላላቆችና ታናናሾች እንስሶች አሉ።
26
በዚያ ጊዜ መርከቦች ይሄዳሉ፥ በዚያም ላይ የፈጠርኸው ዘንዶ ይጫወትበታል።
27
ምግባቸውን በየጊዜው ትሰጣቸው ዘንድ እነዚህ ሁሉ አንተን ተስፋ ያደርጋሉ።
28
በሰጠሃቸውም ጊዜ ይሰበስባሉ፤ እጅህን ትከፍታለህ፥ ከመልካም ነገርም ይጠግባሉ።
29
ፊትህን ስትሰውር ይደነግጣሉ፤ ነፍሳቸውን ታወጣለህ ይሞታሉም፥ ወደ አፈራቸውም ይመለሳሉ።
30
መንፈስህን ትልካለህ ይፈጠራሉም፥ የምድርንም ፊት ታድሳለህ።
31
የእግዚአብሔር ክብር ለዘላለም ይሁን፤ እግዚአብሔር በሥራው ደስ ይለዋል።
32
ምድርን ያያል እንድትንቀጠቀጥም ያደርጋል፤ ተራሮችን ይዳስሳል ይጤሳሉም።
33
በሕይወቴ ሳለሁ ለእግዚአብሔር እቀኛለሁ፥ ለአምላኬም በምኖርበት ዘመን ሁሉ እዘምራለሁ።
34
ቃሌ ለእርሱ ይጣፍጠው፥ እኔም በእግዚአብሔር ደስ ይለኛል።
35
ኅጥኣን ከምድር ይጥፉ፤ ዓመፀኞች እንግዲህ አይገኙ። ነፍሴ ሆይ፥ እግዚአብሔርን ባርኪ። ሃሌ ሉያ።

1
Bless Yahweh, my soul. Yahweh, my God, you are very great. You are clothed with honor and majesty.
2
He covers himself with light as with a garment. He stretches out the heavens like a curtain.
3
He lays the beams of his chambers in the waters. He makes the clouds his chariot. He walks on the wings of the wind.
4
He makes his messengers winds; his servants flames of fire.
5
He laid the foundations of the earth, that it should not be moved forever.
6
You covered it with the deep as with a cloak. The waters stood above the mountains.
7
At your rebuke they fled. At the voice of your thunder they hurried away.
8
The mountains rose, the valleys sank down, to the place which you had assigned to them.
9
You have set a boundary that they may not pass over; that they don''t turn again to cover the earth.
10
He sends forth springs into the valleys. They run among the mountains.
11
They give drink to every animal of the field. The wild donkeys quench their thirst.
12
The birds of the sky nest by them. They sing among the branches.
13
He waters the mountains from his chambers. The earth is filled with the fruit of your works.
14
He causes the grass to grow for the livestock, and plants for man to cultivate, that he may bring forth food out of the earth:
15
wine that makes glad the heart of man, oil to make his face to shine, and bread that strengthens man''s heart.
16
Yahweh''s trees are well watered, the cedars of Lebanon, which he has planted;
17
where the birds make their nests. The stork makes its home in the fir trees.
18
The high mountains are for the wild goats. The rocks are a refuge for the rock badgers.
19
He appointed the moon for seasons. The sun knows when to set.
20
You make darkness, and it is night, in which all the animals of the forest prowl.
21
The young lions roar after their prey, and seek their food from God.
22
The sun rises, and they steal away, and lay down in their dens.
23
Man goes forth to his work, to his labor until the evening.
24
Yahweh, how many are your works! In wisdom have you made them all. The earth is full of your riches.
25
There is the sea, great and wide, in which are innumerable living things, both small and large animals.
26
There the ships go, and leviathan, whom you formed to play there.
27
These all wait for you, that you may give them their food in due season.
28
You give to them; they gather. You open your hand; they are satisfied with good.
29
You hide your face: they are troubled; you take away their breath: they die, and return to the dust.
30
You send forth your Spirit: they are created. You renew the face of the ground.
31
Let the glory of Yahweh endure forever. Let Yahweh rejoice in his works.
32
He looks at the earth, and it trembles. He touches the mountains, and they smoke.
33
I will sing to Yahweh as long as I live. I will sing praise to my God while I have any being.
34
Let your meditation be sweet to him. I will rejoice in Yahweh.
35
Let sinners be consumed out of the earth. Let the wicked be no more. Bless Yahweh, my soul. Praise Yah!