1
አቤቱ፥ ስለ ምን ለዘወትር ጣልኸኝ? በማሰማርያህ በጎች ላይስ ቍጣህን ስለ ምን ተቈጣህ?
2
አስቀድመህ የፈጠርሃትን ማኅበርህን፥ የተቤዤሃትንም የርስትህን በትር፥ በእርስዋ ያደርህባትን የጽዮንን ተራራ አስብ።
3
ጠላት በቅዱሳንህ ላይ እንደ ከፋ መጠን፥ ሁልጊዜም በትዕቢታቸው ላይ እጅህን አንሣ።
4
ጠላቶችህ በበዓል መካከል ተመኩ፤ የማያውቁትንም ምልክት ምልክታቸው አደረጉ።
5
እንደ ላይኛው መግቢያ ውስጥ በዱር እንዳሉም እንጨቶች፥ በመጥረቢያ በሮችዋን ሰበሩ።
6
እንዲሁ በመጥረቢያና በመዶሻ ሰበሩአት።
7
መቅደስህን በእሳት አቃጠሉ፤ የስምህንም ማደሪያ በምድር ውስጥ አረከሱ።
8
አንድ ሆነው በልባቸው በየሕዝባቸው። ኑ፥ የእግዚአብሔርን በዓሎች ከምድር እንሻር አሉ።
9
ምልክታችንን አናይም ከእንግዲህ ወዲህም ነቢይ የለም፤ እስከ መቼ እንዲኖር የሚያውቅ በኛ ዘንድ የለም።
10
አቤቱ፥ ጠላት እስከ መቼ ይሳደባል? ስምህን ጠላት ሁልጊዜ ያቃልላልን?
11
ቀኝህንም በብብትህ መካከል፥ እጅህንም ፈጽመህ ለምን ትመልሳለህ?
12
እግዚአብሔር ግን ከዓለም አስቀድሞ ንጉሥ ነው፥ በምድርም መካከል መድኃኒትን አደረገ።
13
አንተ ባሕርን በኃይልህ አጸናሃት፤ አንተ የእባቦችን ራስ በውኃ ውስጥ ሰበርህ።
14
አንተም የዘንዶውን ራሶች ቀጠቀጥህ፤ ለኢትዮጵያ ሰዎችም ምግባቸውን ሰጠሃቸው።
15
አንተ ምንጮቹንና ፈሳሾቹን ሰነጠቅህ፤ አንተ ሁልጊዜ የሚፈስሱትን ወንዞች አደረቅህ።
16
ቀኑ የአንተ ነው ሌሊቱም የአንተ ነው፤ አንተ ፀሓዩንና ጨረቃውን አዘጋጀህ።
17
አንተ የምድርን ዳርቻ ሁሉ ሠራህ፤ በጋንም ክረምትንም አንተ አደረግህ።
18
ይህን ፍጥረትህን አስብ። ጠላት እግዚአብሔርን ተላገደ፥ ሰነፍ ሕዝብም ስሙን አስቈጣ።
19
የምትገዛልህን ነፍስ ለአራዊት አትስጣት፤ የችግረኞችህን ነፍስ ለዘወትር አትርሳ።
20
ወደ ኪዳንህ ተመልከት፥ የምድር የጨለማ ስፍራዎች በኅጥኣን ቤቶች ተሞልተዋልና።
21
ችግረኛ አፍሮ አይመለስ፤ ችግረኛና ምስኪን ስምህን ያመሰግናሉ።
22
አቤቱ፥ ተነሥ በቀልህንም ተበቀል፤ ሰነፎች ሁልጊዜም የተላገዱህን አስብ።
23
የባሪያዎችህን ቃል አትርሳ፤ የጠላቶችህ ኵራት ሁልጊዜ ወደ አንተ ይወጣል።

1
<> God, why have you rejected us forever? Why does your anger smolder against the sheep of your pasture?
2
Remember your congregation, which you purchased of old, which you have redeemed to be the tribe of your inheritance; Mount Zion, in which you have lived.
3
Lift up your feet to the perpetual ruins, all the evil that the enemy has done in the sanctuary.
4
Your adversaries have roared in the midst of your assembly. They have set up their standards as signs.
5
They behaved like men wielding axes, cutting through a thicket of trees.
6
Now they break all its carved work down with hatchet and hammers.
7
They have burned your sanctuary to the ground. They have profaned the dwelling place of your Name.
8
They said in their heart, "We will crush them completely." They have burned up all the places in the land where God was worshiped.
9
We see no miraculous signs. There is no longer any prophet, neither is there among us anyone who knows how long.
10
How long, God, shall the adversary reproach? Shall the enemy blaspheme your name forever?
11
Why do you draw back your hand, even your right hand? Take it out of your pocket and consume them!
12
Yet God is my King of old, working salvation in the midst of the earth.
13
You divided the sea by your strength. You broke the heads of the sea monsters in the waters.
14
You broke the heads of Leviathan in pieces. You gave him as food to people and desert creatures.
15
You opened up spring and stream. You dried up mighty rivers.
16
The day is yours, the night is also yours. You have prepared the light and the sun.
17
You have set all the boundaries of the earth. You have made summer and winter.
18
Remember this, that the enemy has mocked you, Yahweh. Foolish people have blasphemed your name.
19
Don''t deliver the soul of your dove to wild beasts. Don''t forget the life of your poor forever.
20
Honor your covenant, for haunts of violence fill the dark places of the earth.
21
Don''t let the oppressed return ashamed. Let the poor and needy praise your name.
22
Arise, God! Plead your own cause. Remember how the foolish man mocks you all day.
23
Don''t forget the voice of your adversaries. The tumult of those who rise up against you ascends continually.