1
የእስራኤል ንጉሥ የዳዊት ልጅ የሰሎሞን ምሳሌዎች፤
2
ጥበብንና ተግሣጽን ለማወቅ፥ የእውቀትንም ቃል ለማስተዋል፥
3
የጥበብን ትምህርት ጽድቅንና ፍርድን ቅንነትንም ለመቀበል፥
4
ብልሃትን ለአላዋቂዎች ይሰጥ ዘንድ ለጐበዛዝትም እውቀትንና ጥንቃቄን፥
5
ጠቢብ እነዚህን ከመስማት ጥበብን ይጨምራል፥ አስተዋይም መልካም ምክርን ገንዘቡ ያደርጋል።
6
ምሳሌንና ትርጓሜን የጠቢባንና ቃልና የተሸሸገውን ነገር ለማስተዋል።
7
የጥበብ መጀመሪያ እግዚአብሔርን መፍራት ነው፤ ሰነፎች ግን ጥበብንና ተግሣጽን ይንቃሉ።
8
ልጄ ሆይ፥ የአባትህን ምክር ስማ፥ የእናንትህንም ሕግ አትተው፤
9
ለራስህ የሞገስ ዘውድ ለአንገትህም ድሪ ይሆንልሃልና።
10
ልጄ ሆይ፥ ኃጢአተኞች ቢያባብሉህ እሺ አትበል።
11
ደምን ለማፍሰስ ለእኛ ጋር ና እናድባ፥ ለንጹሕም ያለ ምክንያት ወጥመድን እንሸምቅበት ቢሉ፤
12
በሕይወታቸው ሳሉ እንደ ሲኦል ሆነን እንዋጣቸው፥ በሙሉም ወደ ጕድጓድ እንደሚወድቁ ይሁኑ፤
13
መልካሙን ሀብት ሁሉ እናገኛለን፥ ከምርኮውም ቤታችንን እንሞላለን፤
14
ዕጣህን ከእኛ ጋር ጣል፤ ለሁላችንም አንድ ከረጢት ይሁን ቢሉ፤
15
ልጄ ሆይ፥ ከእነርሱ ጋር በመንገድ አትሂድ፥ ከጎዳናቸውም እግርህን ፈቀቅ አድርግ፤
16
እግሮቻቸው ወደ ክፋት ይሮጣሉና፥ ደም ለማፍሰስም ይፈጥናሉና።
17
መርበብ በወፎች ዓይን ፊት በከንቱ ትተከላለችና።
18
እነርሱም በደማቸው ላይ ያደባሉ፥ በነፍሳቸውም ላይ ይሸምቃሉ።
19
እንዲሁ ይህ መንገድ ትርፍን ለማግኘት የሚሳሳ ሁሉ ነው። የባለቤቱን ነፍስ ይነጥቃል።
20
ጥበብ በጎዳና ትጮኻለች፤ በአደባባይ ድምፅዋን ከፍ ታደርጋለች፤
21
በአደባባይ ትጣራለች፤ በከተማይቱ መግቢያ በር ቃልን ትናገራለች።
22
እናንተ አላዋቂዎች፥ እስከ መቼ አላዋቂነት ትወድዳላችሁ? ፌዘኞችም ፌዝን ይፈቅዳሉ? ሰነፎችም እውቀትን ይጠላሉ?
23
ወደ ዘለፋዬ ተመለሱ፤ እነሆ፥ መንፈሴን አፈስስላችኋለሁ፤ ቃሌን አስተምራችኋለሁ።
24
በጠራሁ ጊዜ እምቢ ስላላችሁ፥ እጄን በዘረጋሁ ጊዜ ማንም ስላላስተዋለ፥
25
ምክሬን ሁሉ ግን ቸል ስላላችሁ፥ ዘለፋዬንም ስላልፈቀዳችሁ፤
26
እኔም ስለዚህ በጥፋታችሁ እስቃለሁ፤ ጥፋታችሁም በመጣ ጊዜ አላግጥባችvሁ።
27
ድንጋጤ እንደ ጐርፍ በደረሰባችሁ ጊዜ፥ ጥፋታችሁም እንደ ዐውሎ ነፋስ በመጣ ጊዜ፥ ጭንቅና መከራ በወረደባችሁ ጊዜ።
28
የዚያን ጊዜ ይጠሩኛል፥ እኔ ግን አልመልስም፤ ተግተው ይሹኛል፥ ነገር ግን አያገኙኝም።
29
እውቀትን ጠልተዋልና፥ እግዚአብሔርንም መፍራት አልመረጡምና፤
30
ምክሬን አልፈቀዱምና፥ ዘለፋዬንም ሁሉ ንቀዋልና፤
31
ስለዚህ የመንገዳቸውን ፍሬ ይበላሉ፥ ከራሳቸው ምክር ይጠግባሉ።
32
አላዋቂዎችን ከጥበብ መራቅ ይገድላቸዋልና፥ ሰነፎችንም ቸልተኛ መሆን ያጠፋቸዋልና።
33
የሚሰማኝ ግን በእርጋታ ይቀመጣል፥ ከመከራም ሥጋት ያርፋል።

1
The proverbs of Solomon, the son of David, king of Israel:
2
to know wisdom and instruction; to discern the words of understanding;
3
to receive instruction in wise dealing, in righteousness, justice, and equity;
4
to give prudence to the simple, knowledge and discretion to the young man:
5
that the wise man may hear, and increase in learning; that the man of understanding may attain to sound counsel:
6
to understand a proverb, and parables, the words and riddles of the wise.
7
The fear of Yahweh is the beginning of knowledge; but the foolish despise wisdom and instruction.
8
My son, listen to your father''s instruction, and don''t forsake your mother''s teaching:
9
for they will be a garland to grace your head, and chains around your neck.
10
My son, if sinners entice you, don''t consent.
11
If they say, "Come with us, Let''s lay in wait for blood; let''s lurk secretly for the innocent without cause;
12
let''s swallow them up alive like Sheol, and whole, like those who go down into the pit.
13
We''ll find all valuable wealth. We''ll fill our houses with spoil.
14
You shall cast your lot among us. We''ll all have one purse."
15
My son, don''t walk in the way with them. Keep your foot from their path,
16
for their feet run to evil. They hurry to shed blood.
17
For in vain is the net spread in the sight of any bird:
18
but these lay wait for their own blood. They lurk secretly for their own lives.
19
So are the ways of everyone who is greedy for gain. It takes away the life of its owners.
20
Wisdom calls aloud in the street. She utters her voice in the public squares.
21
She calls at the head of noisy places. At the entrance of the city gates, she utters her words:
22
"How long, you simple ones, will you love simplicity? How long will mockers delight themselves in mockery, and fools hate knowledge?
23
Turn at my reproof. Behold, I will pour out my spirit on you. I will make known my words to you.
24
Because I have called, and you have refused; I have stretched out my hand, and no one has paid attention;
25
but you have ignored all my counsel, and wanted none of my reproof;
26
I also will laugh at your disaster. I will mock when calamity overtakes you;
27
when calamity overtakes you like a storm, when your disaster comes on like a whirlwind; when distress and anguish come on you.
28
Then will they call on me, but I will not answer. They will seek me diligently, but they will not find me;
29
because they hated knowledge, and didn''t choose the fear of Yahweh.
30
They wanted none of my counsel. They despised all my reproof.
31
Therefore they will eat of the fruit of their own way, and be filled with their own schemes.
32
For the backsliding of the simple will kill them. The careless ease of fools will destroy them.
33
But whoever listens to me will dwell securely, and will be at ease, without fear of harm."