1
እግዚአብሔር ለቀባሁት፥ አሕዛብንም በፊቱ አስገዛ ዘንድ የነገሥታትንም ወገብ እፈታ ዘንድ፥ በሮቹም እንዳይዘጉ መዝጊያዎቹን በፊቱ እከፍት ዘንድ፥ ቀኝ እጁን ለያዝሁት ለቂሮስ እንዲህ ይላል።
2
በፊትህ እሄዳለሁ ተራሮችንም ትክክል አደርጋለሁ፥ የናሱንም ደጆች እሰብራለሁ የብረቱንም መወርወሪያዎች እቈርጣለሁ፤
3
በስምህም የምጠራህ የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር እኔ እንደ ሆንሁ ታውቅ ዘንድ በጨለማ የነበረችውን መዝገብ በስውርም የተደበቀችውን ሀብት እሰጥሃለሁ።
4
ስለ ባሪያዬ ስለ ያዕቆብ፥ ስለ መረጥሁትም ስለ እስራኤል ብዬ በስምህ ጠርቼሃለሁ፤ በቍልምጫ ስምህ ጠራሁህ፥ አንተ ግን አላወቅኸኝም።
5-6
እኔ እግዚአብሔር ነኝ ከእኔም ሌላ ማንም የለም፤ ከእኔም በቀር አምላክ የለም፤ በፀሐይ መውጫና በምዕራብ ያሉ ከእኔ በቀር ማንም ሌላ እንደሌለ ያውቁ ዘንድ አስታጠቅሁህ፥ አንተ ግን አላወቅኸኝም፤ እኔ እግዚአብሔር ነኝ፥ ከእኔም ሌላ ማንም የለም።
7
ብርሃንን ሠራሁ፥ ጨለማውንም ፈጠርሁ፤ ደኅንነትን እሠራለሁ፥ ክፋትንም እፈጥራለሁ፤ እነነዚህን ሁሉ ያደረግሁ እግዚአብሔር እኔ ነኝ።
8
እናንተ ሰማያት ከላይ አንጠባጥቡ ደመናትም ጽድቅን ያዝንቡ፤ ምድርም ትከፈት መድኃኒትንም ታብቅል፥ ጽድቅም በአንድነት ይብቀል፤ እኔ እግዚአብሔር ፈጥሬዋለሁ።
9
ከሠሪው ጋር ለሚታገል ወዮለት! በምድር ሸክላዎች መካከል ያለ ሸክላ ነው። ጭቃ ሠሪውን። ምን ትሠራለህ? ወይስ ሥራህ። እጅ የለውም ይላልን?
10
አባትን። ምን ወልደሃል? ወይም ሴትን። ምን አማጥሽ? ለሚል ወዮ!
11
የእስራኤል ቅዱስ ሠሪውም እግዚአብሔር እንዲህ ይላል። ስለሚመጣው ነገር ጠይቁኝ፥ ስለ ልጆቼና ስለ እጄ ሥራም እዘዙኝ።
12
እኔ ምድርን ሠርቻለሁ ሰውንም በእርስዋ ላይ ፈጥሬአለሁ፤ እኔ በእጄ ሰማያትን ዘርግቼአለሁ፥ ሠራዊታቸውንም ሁሉ አዝዣለሁ።
13
እኔ በጽድቅ አስነሥቼዋለሁ መንገዱንም ሁሉ አቀናለሁ፤ እርሱ ከተማዬን ይሠራል፥ በዋጋም ወይም በደመወዝ ሳይሆን ምርኮኞቼን ያወጣል፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር።
14
እግዚአብሔርም እንዲህ ይላል። የግብጽ ድካምና የኢትዮጵያ ንግድ ቁመተ ረጅሞችም የሳባ ሰዎች ወደ አንተ ያልፋሉ፤ ለአንተም ይሆናሉ እጆቻቸውም ታስረው ይከተሉሃል፤ በፊትህም ያልፋሉ፥ ለአንተም እየሰገዱ። በእውነት እግዚአብሔር በአንተ አለ፥ ከእርሱም ሌላ አምላክ የለም ብለው ይለምኑሃል።
15
የእስራኤል አምላክ መድኃኒት ሆይ፥ በእውነት አንተ ራስህን የምትሰውር አምላክ ነህ።
16
ሁሉም ያፍራሉ ይዋረዱማል፥ ጣዖታትንም የሚሠሩ በአንድነት ወደ ውርደት ይሄዳሉ።
17
እግዚአብሔር ግን እስራኤልን በዘላለማዊ መድኃኒት ያድነዋል፥ እናንተም ለዘላለም አታፍሩምና አትዋረዱም።
18
ሰማያትን የፈጠረ እግዚአብሔር፥ እርሱም ምድርን የሠራና ያደረገ ያጸናትም፥ መኖሪያም ልትሆን እንጂ ለከንቱ እንድትሆን ያልፈጠራት አምላክ፥ እንዲህ ይላል። እኔ እግዚአብሔር ነኝ ከእኔም በቀር ሌላ የለም።
19
በስውር ወይም በጨለማ ምድር ስፍራ አልተናገርሁም፤ ለያዕቆብ ዘር። በከንቱ ፈልጉኝ አላልሁም፤ እኔ እግዚአብሔር ጽድቅን እናገራለሁ ቅንንም አወራለሁ።
20
እናንተ ከአሕዛብ ወገን ሆናችሁ ያመለጣችሁ፥ ተሰብስባችሁ ኑ በአንድነትም ቅረቡ፤ የተቀረጸውን የምስላቸውን እንጨት የሚሸከሙና ያድን ዘንድ ወደማይችል አምላክ የሚጸልዩ እውቀት የላቸውም።
21
ይናገሩ ይቅረቡም በአንድነትም ይማከሩ፤ ከጥንቱ ይህን ያሳየ ከቀድሞስ የተናገረ ማን ነው? ያሳየሁም የተናገርሁም እኔ እግዚአብሔር አይደለሁምን? ከእኔም በቀር ሌላ አምላክ የለም፤ እኔ ጻድቅ አምላክና መድኃኒት ነኝ፥ ከእኔም በቀር ማንም የለም።
22
እናንተ የምድር ዳርቻ ሁሉ፥ እኔ አምላክ ነኝና፥ ከእኔም በቀር ሌላ የለምና ወደ እኔ ዘወር በሉ ትድኑማላችሁ።
23
ቃሌ ከአፌ በጽድቅ ወጥታለች፥ አትመለስም። ጕልበት ሁሉ ለእኔ ይንበረከካል፥ ምላስም ሁሉ በእኔ ይምላል ብዬ በራሴ ምያለሁ።
24
ስለ እኔም። በእግዚአብሔር ዘንድ ብቻ ጽድቅና ኃይል አለ፥ ወደ እርሱም ሰዎች ይመጣሉ፥ በእርሱም ላይ የተቈጡ ሁሉ ያፍራሉ።
25
የእስራኤልም ዘር ሁሉ በእግዚአብሔር ይጸድቃሉ፥ ይመካሉም ይባላል።

1
Thus says Yahweh to his anointed, to Cyrus, whose right hand I have held, to subdue nations before him, and strip kings of their armor; to open the doors before him, and the gates shall not be shut:
2
"I will go before you, and make the rough places smooth. I will break the doors of brass in pieces, and cut apart the bars of iron.
3
I will give you the treasures of darkness, and hidden riches of secret places, that you may know that it is I, Yahweh, who call you by your name, even the God of Israel.
4
For Jacob my servant''s sake, and Israel my chosen, I have called you by your name. I have surnamed you, though you have not known me.
5
I am Yahweh, and there is none else. Besides me, there is no God. I will strengthen you, though you have not known me;
6
that they may know from the rising of the sun, and from the west, that there is none besides me. I am Yahweh, and there is no one else.
7
I form the light, and create darkness. I make peace, and create calamity. I am Yahweh, who does all these things.
8
Distil, you heavens, from above, and let the skies pour down righteousness. Let the earth open, that it may bring forth salvation, and let it cause righteousness to spring up with it. I, Yahweh, have created it.
9
Woe to him who strives with his Maker--a clay pot among the clay pots of the earth! Shall the clay ask him who fashions it, ''What are you making?'' or your work, ''He has no hands?''
10
Woe to him who says to a father, ''What have you become the father of?'' or to a mother, ''To what have you given birth?''"
11
Thus says Yahweh, the Holy One of Israel, and his Maker: "You ask me about the things that are to come, concerning my sons, and you command me concerning the work of my hands!
12
I have made the earth, and created man on it: I, even my hands, have stretched out the heavens; and all their army have I commanded.
13
I have raised him up in righteousness, and I will make straight all his ways: he shall build my city, and he shall let my exiles go free, not for price nor reward, says Yahweh of Armies.
14
Thus says Yahweh: "The labor of Egypt, and the merchandise of Ethiopia, and the Sabeans, men of stature, shall come over to you, and they shall be yours. They shall go after you. In chains they shall come over; and they shall fall down to you. They shall make supplication to you: ''Surely God is in you; and there is none else, there is no other god.
15
Most certainly you are a God who hid yourself, God of Israel, the Savior.''"
16
They shall be disappointed, yes, confounded, all of them; they shall go into confusion together who are makers of idols.
17
[But] Israel shall be saved by Yahweh with an everlasting salvation: you shall not be disappointed nor confounded world without end.
18
For thus says Yahweh who created the heavens, the God who formed the earth and made it, who established it and didn''t create it a waste, who formed it to be inhabited: I am Yahweh; and there is no one else.
19
I have not spoken in secret, in a place of the land of darkness; I didn''t say to the seed of Jacob, Seek you me in vain: I, Yahweh, speak righteousness, I declare things that are right.
20
Assemble yourselves and come; draw near together, you who have escaped from the nations: they have no knowledge who carry the wood of their engraved image, and pray to a god that can''t save.
21
Declare you, and bring [it] forth; yes, let them take counsel together: who has shown this from ancient time? who has declared it of old? Haven''t I, Yahweh? and there is no God else besides me, a just God and a Savior; there is no one besides me.
22
Look to me, and be you saved, all the ends of the earth; for I am God, and there is none else.
23
By myself have I sworn, the word is gone forth from my mouth [in] righteousness, and shall not return, that to me every knee shall bow, every tongue shall swear.
24
Only in Yahweh, it is said of me, is righteousness and strength; even to him shall men come; and all those who were incensed against him shall be disappointed.
25
In Yahweh shall all the seed of Israel be justified, and shall glory.