1
እስራኤል ሆይ፥ ብትመለስ፥ ወደ እኔ ተመለስ፥ ይላል እግዚአብሔር፤ ርkWsvትህንም ከፊቴ ብታስወግድ፥ ባትናወጥም፥
2
ሕያው እግዚአብሔርን! ብለህም በእውነትና በቅንነት በጽድቅም ብትምል፥ አሕዛብ በእርሱ ይባረካሉ በእርሱም ይመካሉ።
3
እግዚአብሔር ለይሁዳና ለኢየሩሳሌም ሰዎች እንዲህ ይላልና። ጥጋቱን እርሻ እረሱ በእሾህም ላይ አትዝሩ።
4
እናንተም የይሁዳ ሰዎች በኢየሩሳሌምም የምትኖሩ ሆይ፥ ስለ ሥራችሁ ክፋት KWTaዬ እንደ እሳት እንዳይወጣ የሚያጠፋውም ሳይኖር እንዳያቃጥል፥ ለእግዚአብሔር ተገረዙ፥ የልባችሁንም ሸለፈት አስወግዱ።
5
በይሁዳ ዘንድ ተናገሩ በኢየሩሳሌምም ላይ አውሩና። በአገሪቱ ላይ መለከት ንፉ በሉ፤ ጮኻችሁም። ሁላችሁ ተሰብሰቡ ወደ ተመሸጉትም ከተሞች እንግባ በሉ።
6
ከሰሜን ክፉ ነገርንና ጽኑ ጥፋትን አመጣለሁና ወደ ጽዮን ዓላማን አንሡ፤ ሽሹ፥ አትዘግዩ።
7
አንበሳ ከጭፍቅ ዱር ወጥቶአል፥ አሕዛብንም የሚዘርፍ ተነሥቶአል፤ ምድርሽን ባድማ ያደርግ ዘንድ ከስፍራው ወጥቶአል፥ ከተሞችሽም ሰው የሌለባቸው ፍርስራሾች ይሆናሉ።
8
የእግዚአብሔር ጽኑ KWTa ከእኛ ዘንድ አልተመለሰምና ማቅ ልበሱ፥ አልቅሱም ዋይም በሉ።
9
በዚያም ቀን፥ ይላል እግዚአብሔር፥ የንጉሡና የመኳንንቱ ልብ ይጠፋል፥ ካህናቱም ይደነቃሉ ነቢያቱም ይደነግጣሉ።
10
እኔም። ጌታ እግዚአብሔር ሆይ፥ ወዮ፥ አንተ ሰይፍ እስከ ነፍስ ድረስ በደረሰ ጊዜ። ሰላም ይሆንላችኋል ብለህ ይህን ሕዝብና ኢየሩሳሌምን እጅግ አታለልህ አልሁ።
11
በዚያ ጊዜ ለዚህ ሕዝብና ለኢየሩሳሌም። ለማበጠር ወይም ለማጥራት ሳይሆን የሚያቃጥል ነፋስ በምድረ በዳ ካሉ ከወናዎች ኮረብቶች ወደ ወገኔ ሴት ልጅ ይመጣል፤
12
ስለ እኔ ጽኑ የሆነ ነፋስ ከእነዚህ ይመጣል ይባላል። አሁንም እኔ ደግሞ ፍርዴን በእነርሱ ላይ እናገራለሁ።
13
እነሆ፥ እንደ ደመና ይወጣል፥ ሰረገሎቹም እንደ ዐውሎ ነፋስ፤ ፈረሶቹም ከንስር ይልቅ ፈጣኖች ናቸው። ጠፍተናልና ወዮልን።
14
ኢየሩሳሌም ሆይ፥ ትድኚ ዘንድ ልብሽን ከክፉ ነገር እጠቢ። ክፉ አሳብ የሚኖርብሽ እስከ መቼ ድረስ ነው?
15
የተናጋሪ ድምፅ ከዳን ዘንድ ይናገራልና፥ ከኤፍሬምም ኮረብቶች መከራን ያወራልና።
16
ለአሕዛብ አሰሙና። እነሆ፥ ጠባቂዎች ከሩቅ አገር ይመጣሉ፤ በይሁዳም ከተሞች ላይ ይጮኻሉ ብላችሁ በኢየሩሳሌም ላይ አውሩ።
17
በእኔ ላይ ዓመፀኛ ሆናለችና በዙሪያዋ ከብበው እንደ እርሻ ጠባቂዎች ሆነውባታል፥ ይላል እግዚአብሔር።
18
መንገድሽና ሥራሽ ይህን አድርጎብሻል፤ ይህ ክፋትሽ መራር ነው፥ ወደ ልብሽም ደርሶአል።
19
አንጀቴ! አንጀቴ! ልቤ በጣም ታምሞአል፥ በውስጤም ልቤ ታውኮብኛል፤ ነፍሴ ሆይ፥ የመለከትን ድምፅና የሰልፍን ውካታ ሰምተሻልና ዝም እል ዘንድ አልችልም።
20
መከራ በመከራ ላይ ተጠርቶአል፤ ምድርም ሁሉ ተበዝብዛለችና፤ በድንገትም ድንኳኔ በቅጽበት ዓይንም መጋረጃዎቼ ጠፉ።
21
ዓላማውን የምመለከት፥ የመለከቱንስ ድምፅ የምሰማ እስከ መቼ ነው?
22
ሕዝቤ ሰንፈዋልና አላወቁኝም፤ ሰነፎች ልጆች ናቸው፥ ማስተዋልም የላቸውም፤ ክፉ ነገርን ለማድረግ ብልሃተኞች ናቸው፥ በጎ ነገርን ማድረግ ግን አያውቁም።
23
ምድሪቱን አየሁ፥ እነሆም፥ ባዶ ነበረች አንዳችም አልነበረባትም፤ ሰማያትንም አየሁ፥ ብርሃንም አልነበረባቸውም።
24
ተራሮችን አየሁ፥ እነሆም፥ ተንቀጠቀጡ፥ ኮረብቶችም ሁሉ ተናወጡ።
25
አየሁ፥ እነሆም፥ ሰው አልነበረም፥ የሰማይም ወፎች ሁሉ ሸሽተው ነበር።
26
አየሁ፥ እነሆም፥ ፍሬያማ እርሻ ምድረ በዳ ሆነች፥ ከተሞችም ሁሉ ከእግዚአብሔር ፊት ከጽኑ KWTaው የተነሣ ፈርሰው ነበር።
27
እግዚአብሔርም እንዲህ ይላል። ምድር ሁሉ ባድማ ትሆናለች፥ ነገር ግን ፈጽሜ አላጠፋትም።
28
ስለዚህ ምድር ታለቅሳለች፥ በላይም ሰማይ ይጠKWraል፤ ተናግሬአለሁና፥ አስቤአለሁም፤ አልጸጸትም ከእርሱም አልመለስም።
29
ከፈረሰኞችና ከቀስተኞች ድምፅ የተነሣ ከተማ ሁሉ ሸሽታለች፤ ወደ ችፍግ ዱርም ይገባሉ በቋጥኝ ላይም ይወጣሉ፤ ከተማ ሁሉ ተለቅቃለች የሚቀመጥባትም ሰው የለም።
30
አንቺም የተበዘበዝሽ ሆይ፥ ምን ታደርጊአለሽ? ቀይ በለበስሽ ጊዜ፥ በወርቅ አንባርም ባጌጥሽ ጊዜ፥ ዓይንሽንም በkWl በተኳልሽ ጊዜ፥ በከንቱ ታጌጫለሽ፤ ውሽሞችሽ አቃለሉሽ፥ ነፍስሽን ይሹአታል።
31
እንደምታምጥ የበkWrዋንም እንደምትወልድ ሴት ድምፅ ሰምቻለሁና፤ የጽዮን ሴት ልጅ ድምፅ በድካም ይሰልላል፥ እጆችዋንም ትዘረጋለችና። ተገድለው ከሞቱት የተነሣ ነፍሴ ዝላለችና ወዮልኝ! አለች።

1
If you will return, Israel, says Yahweh, if you will return to me, and if you will put away your abominations out of my sight; then you shall not be removed;
2
and you shall swear, As Yahweh lives, in truth, in justice, and in righteousness; and the nations shall bless themselves in him, and in him shall they glory.
3
For thus says Yahweh to the men of Judah and to Jerusalem, Break up your fallow ground, and don''t sow among thorns.
4
Circumcise yourselves to Yahweh, and take away the foreskins of your heart, you men of Judah and inhabitants of Jerusalem; lest my wrath go forth like fire, and burn so that none can quench it, because of the evil of your doings.
5
Declare you in Judah, and publish in Jerusalem; and say, Blow you the trumpet in the land: cry aloud and say, Assemble yourselves, and let us go into the fortified cities.
6
Set up a standard toward Zion: flee for safety, don''t stay; for I will bring evil from the north, and a great destruction.
7
A lion is gone up from his thicket, and a destroyer of nations; he is on his way, he is gone forth from his place, to make your land desolate, that your cities be laid waste, without inhabitant.
8
For this gird you with sackcloth, lament and wail; for the fierce anger of Yahweh hasn''t turned back from us.
9
It shall happen at that day, says Yahweh, that the heart of the king shall perish, and the heart of the princes; and the priests shall be astonished, and the prophets shall wonder.
10
Then said I, Ah, Lord Yahweh! surely you have greatly deceived this people and Jerusalem, saying, You shall have peace; whereas the sword reaches to the life.
11
At that time shall it be said to this people and to Jerusalem, A hot wind from the bare heights in the wilderness toward the daughter of my people, not to winnow, nor to cleanse;
12
a full wind from these shall come for me: now will I also utter judgments against them.
13
Behold, he shall come up as clouds, and his chariots [shall be] as the whirlwind: his horses are swifter than eagles. Woe to us! for we are ruined.
14
Jerusalem, wash your heart from wickedness, that you may be saved. How long shall your evil thoughts lodge within you?
15
For a voice declares from Dan, and publishes evil from the hills of Ephraim:
16
make you mention to the nations; behold, publish against Jerusalem, [that] watchers come from a far country, and give out their voice against the cities of Judah.
17
As keepers of a field are they against her round about, because she has been rebellious against me, says Yahweh.
18
Your way and your doings have procured these things to you; this is your wickedness; for it is bitter, for it reaches to your heart.
19
My anguish, my anguish! I am pained at my very heart; my heart is disquieted in me; I can''t hold my peace; because you have heard, O my soul, the sound of the trumpet, the alarm of war.
20
Destruction on destruction is cried; for the whole land is laid waste: suddenly are my tents destroyed, [and] my curtains in a moment.
21
How long shall I see the standard, and hear the sound of the trumpet?
22
For my people are foolish, they don''t know me; they are foolish children, and they have no understanding; they are wise to do evil, but to do good they have no knowledge.
23
I saw the earth, and, behold, it was waste and void; and the heavens, and they had no light.
24
I saw the mountains, and behold, they trembled, and all the hills moved back and forth.
25
I saw, and behold, there was no man, and all the birds of the sky were fled.
26
I saw, and behold, the fruitful field was a wilderness, and all the cities of it were broken down at the presence of Yahweh, [and] before his fierce anger.
27
For thus says Yahweh, The whole land shall be a desolation; yet will I not make a full end.
28
For this shall the earth mourn, and the heavens above be black; because I have spoken it, I have purposed it, and I have not repented, neither will I turn back from it.
29
Every city flees for the noise of the horsemen and archers; they go into the thickets, and climb up on the rocks: every city is forsaken, and not a man dwells therein.
30
You, when you are made desolate, what will you do? Though you clothe yourself with scarlet, though you deck you with ornaments of gold, though you enlarge your eyes with paint, in vain do you make yourself beautiful; [your] lovers despise you, they seek your life.
31
For I have heard a voice as of a woman in travail, the anguish as of her who brings forth her first child, the voice of the daughter of Zion, who gasps for breath, who spreads her hands, [saying], Woe is me now! for my soul faints before the murderers.