1
ለዓመፀኛይቱና ለረከሰች ለአስጨናቂይቱም ከተማ ወዮላት!
2
ድምፅን አልሰማችም፥ ተግሣጽንም አልተቀበለችም፤ በእግዚአብሔርም አልታመነችም፥ ወደ አምላክዋም አልቀረበችም።
3
በውስጥዋ ያሉ አለቆችዋ እንደሚያገሡ አንበሶች ናቸው፤ ፈራጆችዋም እስከ ነገ ድረስ ምንም እንደማያስቀሩ እንደ ማታ ተኵላዎች ናቸው።
4
ነቢያቶችዋ ቅሌታሞችና ተንኰለኞች ሰዎች ናቸው፤ ካህናቶችዋም መቅደሱን አርክሰዋል፥ በሕግም ላይ ግፍ ሠርተዋል።
5
እግዚአብሔር በውስጥዋ ጻድቅ ነው፤ ክፋትን አያደርግም፤ ፍርዱን በየማለዳው ወደ ብርሃን ያወጣል፥ ሳያወጣውም አይቀርም፤ ዓመፀኛው ግን እፍረትን አያውቅም።
6
አሕዛብን አጥፍቻለሁ፤ ግንቦቻቸው ሁሉ ፈርሰዋል፤ መንገዳቸውን ማንም እንዳያልፍባት ምድረ በዳ አድርጌአለሁ፥ ከተሞቻቸውም ማንም እንዳይኖርባቸው፥ አንድስ እንኳ እንዳይቀመጥባቸው ፈርሰዋል።
7
እኔም- ይፈሩኛል፥ ተግሣጽንም ይቀበላሉ፤ ካዘዝኋትም ሁሉ ከዓይንዋ ምንም አይጠፋም ብዬ ነበር፤ እነርሱ ግን በማለዳ ተነሥተው ድርጊታቸውን ሁሉ አረከሱ።
8
መዓቴንና የቍጣዬን ትኵሳት ሁሉ አፈስስባቸው ዘንድ ፍርዴ አሕዛብን ለመሰብሰብ፥ መንግሥታትንም ለማከማቸት ነውና፥ ምድርም ሁሉ በቅንዓቴ እሳት ትበላለችና ስለዚህ ለመበዝበዝ እስከምነሣበት ቀን ድረስ ጠብቁኝ፥ ይላል እግዚአብሔር።
9
በዚያን ጊዜም አሕዛብ ሁሉ አንድ ሆነው እግዚአብሔርን ያገለግሉት ዘንድ ስሙን እንዲጠሩ ንጹሐን ልሳን እመልስላቸዋለሁ።
10
ከኢትዮጵያ ወንዞች ማዶ የሚማልዱኝ፥ የተበተኑት ሴቶች ልጆቼ፥ ቍርባኔን ያመጡልኛል።
11
በዚያን ጊዜ እየታበዩ የሚፎክሩትን ከመካከልሽ አወጣለሁና፥ አንቺም በቅዱስ ተራራዬ ዳግመኛ አትኰሪምና በዚያ ቀን በእኔ ላይ ተላልፈሽ በሠራሽው ሥራ ሁሉ አትፍሪም።
12
በመካከልሽም የዋህና ትሑት ሕዝብን አስቀራለሁ፤ በእግዚአብሔርም ስም ይታመናሉ።
13
የእስራኤል ቅሬታ ኃጢአትን አይሠሩም፥ ሐሰትንም አይናገሩም፥ በአፋቸውም ውስጥ ተንኰለኛ ምላስ አይገኝም፤ እነርሱም ይሰማራሉ፥ ይመሰጉማል፥ የሚያስፈራቸውም የለም።
14
የጽዮን ልጅ ሆይ፥ ዘምሪ፤ እስራኤል ሆይ፥ እልል በል፤ የኢየሩሳሌም ልጅ ሆይ፥ በፍጹም ልብሽ ሐሤት አድርጊ ደስም ይበልሽ።
15
እግዚአብሔር ፍርድሽን አስወግዶአል፥ ጠላትሽንም ጥሎአል፤ የእስራኤል ንጉሥ እግዚአብሔር በመካከልሽ አለ፥ ከእንግዲህም ወዲህ ክፉ ነገርን አታዪም።
16
በዚያን ቀን ለኢየሩሳሌም። ጽዮን ሆይ፥ አትፍሪ፥ እጆችሽም አይዛሉ።
17
አምላክሽ እግዚአብሔር በመካከልሽ ታዳጊ ኃያል ነው፤ በደስታ በአንቺ ደስ ይለዋል፥ በፍቅሩም ያርፋል፥ በእልልታም በአንቺ ደስ ይለዋል ይባላል።
18
ከጉባኤው ርቀው የሚያዝኑትን፥ ከአንቺም የሆኑትን እሰበስባለሁ፤ ስድብ እንደ ሸክም ከብዶባቸው ነበር።
19
በዚያ ዘመን እነሆ፥ ባስጨነቁሽ ሁሉ ላይ አደርግባቸዋለሁ፤ አንካሳይቱንም አድናለሁ፥ የተጣለችውንም እሰበስባታለሁ፤ ባፈሩባትም ምድር ሁሉ ላይ ለምስጋናና ለከበረ ስም አደርጋቸዋለሁ።
20
በዚያ ዘመን አስገባችኋለሁ፥ በዚያም ዘመን እሰበስባችኋለሁ፤ ምርኮአችሁንም በዓይናችሁ ፊት በመለስሁ ጊዜ በምድር አሕዛብ ሁሉ መካከል ለከበረ ስምና ለምስጋና አደርጋችኋለሁ፥ ይላል እግዚአብሔር።

1
Woe to her who is rebellious and polluted, the oppressing city!
2
She didn''t obey the voice. She didn''t receive correction. She didn''t trust in Yahweh. She didn''t draw near to her God.
3
Her princes in the midst of her are roaring lions. Her judges are evening wolves. They leave nothing until the next day.
4
Her prophets are arrogant and treacherous people. Her priests have profaned the sanctuary. They have done violence to the law.
5
Yahweh, in the midst of her, is righteous. He will do no wrong. Every morning he brings his justice to light. He doesn''t fail, but the unjust know no shame.
6
I have cut off nations. Their battlements are desolate. I have made their streets waste, so that no one passes by. Their cities are destroyed, so that there is no man, so that there is no inhabitant.
7
I said, "Just fear me. Receive correction, so that her dwelling won''t be cut off, according to all that I have appointed concerning her." But they rose early and corrupted all their doings.
8
"Therefore wait for me," says Yahweh, "until the day that I rise up to the prey, for my determination is to gather the nations, that I may assemble the kingdoms, to pour on them my indignation, even all my fierce anger, for all the earth will be devoured with the fire of my jealousy.
9
For then I will purify the lips of the peoples, that they may all call on the name of Yahweh, to serve him shoulder to shoulder.
10
From beyond the rivers of Cush, my worshipers, even the daughter of my dispersed people, will bring my offering.
11
In that day you will not be disappointed for all your doings, in which you have transgressed against me; for then I will take away out of the midst of you your proudly exulting ones, and you will no more be haughty in my holy mountain.
12
But I will leave in the midst of you an afflicted and poor people, and they will take refuge in the name of Yahweh.
13
The remnant of Israel will not do iniquity, nor speak lies, neither will a deceitful tongue be found in their mouth, for they will feed and lie down, and no one will make them afraid."
14
Sing, daughter of Zion! Shout, Israel! Be glad and rejoice with all your heart, daughter of Jerusalem.
15
Yahweh has taken away your judgments. He has thrown out your enemy. The King of Israel, Yahweh, is in the midst of you. You will not be afraid of evil any more.
16
In that day, it will be said to Jerusalem, "Don''t be afraid, Zion. Don''t let your hands be slack."
17
Yahweh, your God, is in the midst of you, a mighty one who will save. He will rejoice over you with joy. He will rest in his love. He will rejoice over you with singing.
18
Those who are sad for the appointed feasts, I will remove from you. They are a burden and a reproach to you.
19
Behold, at that time I will deal with all those who afflict you, and I will save those who are lame, and gather those who were driven away. I will give them praise and honor, whose shame has been in all the earth.
20
At that time will I bring you in, and at that time will I gather you; for I will give you honor and praise among all the peoples of the earth, when I bring back your captivity before your eyes, says Yahweh.