1
በዳርዮስ በሁለተኛው ዓመት በስምንተኛው ወር የእግዚአብሔር ቃል ወደ አዶ ልጅ ወደ በራክዩ ልጅ ወደ ነቢዩ ወደ ዘካርያስ እንዲህ ሲል መጣ።
2
እግዚአብሔር በአባቶቻችሁ ላይ እጅግ ተቈጥቶ ነበር።
3
ስለዚህ እንዲህ በላቸው። የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል። ወደ እኔ ተመለሱ፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር፥ እኔም ወደ እናንተ እመለሳለሁ፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር።
4
የቀደሙት ነቢያት ለአባቶቻችሁ እንዲህ ብለው ሰብከዋል። የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል። ከክፉ መንገዳችሁና ከክፉ ሥራችሁ ተመለሱ፤ እነርሱ ግን አልሰሙም፥ እኔንም አላደመጡም፤ እንደ እነርሱ አትሁኑ፥ ይላል እግዚአብሔር።
5
አባቶቻችሁ ወዴት ናቸው? ነቢያትስ ለዘላለም በሕይወት ይኖራሉን?
6
ለባሪያዎቼስ ለነቢያት ያዘዝኋቸው ቃሎቼና ሥርዓቴ በአባቶቻችሁ ላይ አልደረሱምን? እነርሱም ተመልሰው። የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር በመንገዳችንና በሥራችን መጠን ያደርግብን ዘንድ እንዳሰበ እንዲሁ አድርጎብናል አሉ።
7
በዳርዮስ በሁለተኛው ዓመት ሳባጥ በሚባል በአሥራ አንደኛው ወር በሀያ አራተኛው ቀን የእግዚአብሔር ቃል ወደ አዶ ልጅ ወደ በራክዩ ልጅ ወደ ነቢዩ ወደ ዘካርያስ እንዲህ ሲል መጣ።
8
እነሆም፥ አንድ ሰው በመጋላ ፈረስ ተቀምጦ በሌሊት አየሁ፥ እርሱም በሸለቆው ውስጥ ባሉ በባርሰነት ዛፎች መካከል ቆሞ ነበር፤ በስተ ኋላውም መጋላና ሐመር አንባላይም ፈረሶች ነበሩ።
9
እኔም። ጌታዬ ሆይ፥ እነዚህ ምንድር ናቸው? አልሁ። ከእኔም ጋር ይነጋገር የነበረው መልአክ። እነዚህ ምን እንደ ሆኑ አሳይሃለሁ አለኝ።
10
በባርሰነት ዛፎች መካከልም ቆሞ የነበረው ሰው። እነዚህ በምድር ላይ ይመላለሱ ዘንድ እግዚአብሔር የላካቸው ናቸው ብሎ መለሰ።
11
በባርሰነት ዛፎች መካከልም ቆሞ የነበረውን የእግዚአብሔርን መልአክ። በምድር ላይ ተመላለስን፥ እነሆም፥ ምድር ሁሉ ዝም ብላ ዐርፋ ተቀምጣለች ብለው መለሱለት።
12
የእግዚአብሔርም መልአክ መልሶ። አቤቱ፥ የሠራዊት ጌታ ሆይ፥ እነዚህ ሰባ ዓመት የተቈጣሃቸውን ኢየሩሳሌምንና የይሁዳን ከተሞች የማትምራቸው እስከ መቼ ነው? አለ።
13
እግዚአብሔርም መልሶ ከእኔ ጋር ይነጋገር ለነበረው መልአክ በመልካምና በሚያጽናና ቃል ተናገረው።
14
ስለዚህም ከእኔ ጋር ይነጋገር የነበረው መልአክ እንዲህ አለኝ። ስበክ እንዲህም በል። የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል። እኔ በታላቅ ቅንዓት በኢየሩሳሌምና በጽዮን ቀንቻለሁ።
15
እኔ ጥቂት ብቻ ተቈጥቼ ሳለሁ እነርሱ ክፋትን ስላገዙት፥ ባልተቸገሩት አሕዛብ ላይ እጅግ ተቈጥቻለሁ።
16
ስለዚህ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል። ወደ ኢየሩሳሌም በምሕረት ተመልሻለሁ፤ ቤቴ ይሠራባታል፤ በኢየሩሳሌምም ላይ ገመድ ይዘረጋበታል፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር።
17
ደግሞም እንዲህ ስትል ስበክ። የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል። ከተሞቼ ደግሞ በበጎ ነገር ይረካሉ፤ እግዚአብሔርም ደግሞ ጽዮንን ያጽናናል፥ ኢየሩሳሌምንም ደግሞ ይመርጣል።
18
ዓይኖቼንም አንሥቼ እነሆ፥ አራት ቀንዶች አየሁ።
19
ከእኔም ጋር ይነጋገር የነበረውን መልአክ። እነዚህ ምንድር ናቸው? አልሁት። እርሱም። እነዚህ ይሁዳንና እስራኤልን ኢየሩሳሌምንም የበተኑ ቀንዶች ናቸው ብሎ መለሰልኝ።
20
እግዚአብሔርም አራት ጠራቢዎች አሳየኝ።
21
እኔም። እነዚህ የመጡት ምን ሊሠሩ ነው? አልሁ። እርሱም። አንድ ሰው ራሱን እስከማያነሣ ድረስ እነዚህ ቀንዶች ይሁዳን የበተኑ ናቸው፤ እነዚህ ግን ሊያስፈራሩአቸው፥ የይሁዳንም አገር ይበትኑ ዘንድ ቀንዳቸውን ያነሡትን የአሕዛብን ቀንዶች ሊጥሉ መጥተዋል ብሎ ተናገረ።

1
In the eighth month, in the second year of Darius, the word of Yahweh came to Zechariah the son of Berechiah, the son of Iddo, the prophet, saying,
2
"Yahweh was very displeased with your fathers.
3
Therefore tell them: Thus says Yahweh of Armies: ''Return to me,'' says Yahweh of Armies, ''and I will return to you,'' says Yahweh of Armies.
4
Don''t you be like your fathers, to whom the former prophets proclaimed, saying: Thus says Yahweh of Armies, ''Return now from your evil ways, and from your evil doings;'' but they did not hear, nor listen to me, says Yahweh.
5
Your fathers, where are they? And the prophets, do they live forever?
6
But my words and my decrees, which I commanded my servants the prophets, didn''t they overtake your fathers? "Then they repented and said, ''Just as Yahweh of Armies determined to do to us, according to our ways, and according to our practices, so he has dealt with us.''"
7
On the twenty-fourth day of the eleventh month, which is the month Shebat, in the second year of Darius, the word of Yahweh came to Zechariah the son of Berechiah, the son of Iddo, the prophet, saying,
8
"I had a vision in the night, and behold, a man riding on a red horse, and he stood among the myrtle trees that were in a ravine; and behind him there were red, brown, and white horses.
9
Then I asked, ''My lord, what are these?''" The angel who talked with me said to me, "I will show you what these are."
10
The man who stood among the myrtle trees answered, "They are the ones Yahweh has sent to go back and forth through the earth."
11
They reported to the angel of Yahweh who stood among the myrtle trees, and said, "We have walked back and forth through the earth, and behold, all the earth is at rest and in peace."
12
Then the angel of Yahweh replied, "O Yahweh of Armies, how long will you not have mercy on Jerusalem and on the cities of Judah, against which you have had indignation these seventy years?"
13
Yahweh answered the angel who talked with me with kind and comforting words.
14
So the angel who talked with me said to me, "Proclaim, saying, ''Thus says Yahweh of Armies: "I am jealous for Jerusalem and for Zion with a great jealousy.
15
I am very angry with the nations that are at ease; for I was but a little displeased, but they added to the calamity."
16
Therefore thus says Yahweh: "I have returned to Jerusalem with mercy. My house shall be built in it," says Yahweh of Armies, "and a line shall be stretched forth over Jerusalem."''
17
"Proclaim further, saying, ''Thus says Yahweh of Armies: "My cities will again overflow with prosperity, and Yahweh will again comfort Zion, and will again choose Jerusalem."''"
18
I lifted up my eyes, and saw, and behold, four horns.
19
I asked the angel who talked with me, "What are these?" He answered me, "These are the horns which have scattered Judah, Israel, and Jerusalem."
20
Yahweh showed me four craftsmen.
21
Then I asked, "What are these coming to do?" He said, "These are the horns which scattered Judah, so that no man lifted up his head; but these have come to terrify them, to cast down the horns of the nations, which lifted up their horn against the land of Judah to scatter it."