1
በሚልክያስ እጅ ለእስራኤል የሆነ የእግዚአብሔር ቃል ሸክም ይህ ነው።
2
ወድጃችኋለሁ፥ ይላል እግዚአብሔር፤ እናንተ ግን። በምን ወደድኸን? ብላችኋል። ዔሳው የያዕቆብ ወንድም አልነበረምን? ይላል እግዚአብሔር፤ ያዕቆብንም ወደድሁ፥ ዔሳውንም ጠላሁ፤
3
ተራሮቹንም በረሃ አደረግኋቸው፥ ርስቱንም ለምድረ በዳ ቀበሮች አሳልፌ ሰጠኋቸው።
4
ኤዶምያስ። እኛ ፈርሰናል፥ ነገር ግን የፈረሰውን መልሰን እንሠራለን ቢል፥ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል። እነርሱ ይሠራሉ፥ እኔ ግን አፈርሳለሁ፤ በሰዎችም ዘንድ። የበደል ዳርቻና እግዚአብሔር ለዘላለም የተቈጣው ሕዝብ ይባላል።
5
ዓይኖቻችሁም ያያሉ፥ እናንተም። እግዚአብሔር ከእስራኤል ዳርቻ ወዲያ ታላቅ ይሁን ትላላችሁ።
6
እናንተ ስሜን የምታቃልሉ ካህናት ሆይ፥ ልጅ አባቱን፥ ባሪያም ጌታውን ያከብራል፤ እኔስ አባት ከሆንሁ ክብሬ ወዴት አለ? ጌታስ ከሆንሁ መፈራቴ ወዴት አለ? ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር። እናንተም። ስምህን ያቃለልን በምንድር ነው? ብላችኋል።
7
በመሠዊያዬ ላይ ርኩስ እንጀራ ታቀርባላችሁ። እናንተም። ያረከስንህ በምንድር ነው? ብላችኋል። የእግዚአብሔር ገበታ የተነቀፈ ነው በማለታችሁ ነው።
8
ዕውር መሥዋዕትንም ስታቀርቡ ይህ ክፉ አይደለምን? አንካሳውንና የታመመውን ስታቀርቡ ይህ ክፉ አይደለምን? ያንን ለአለቃህ አቅርብ፤ በውኑ በአንተ ደስ ይለዋልን? ወይስ ፊትህን ይቀበላልን? ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር።
9
አሁንም ጸጋን ይሰጠን ዘንድ እግዚአብሔርን ለምኑ፤ ይህ ከእጃችሁ የተሰጠ ሲሆን ከቶ ፊታችሁን ይቀበላልን? ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር።
10
በመሠዊያዬ ላይ እሳትን በከንቱ እንዳታቃጥሉ ከእናንተ ዘንድ ደጅ የሚዘጋ ሰው ምነው በተገኘ! በእናንተ ደስ አይለኝም፥ ቍርባንንም ከእጃችሁ አልቀበልም፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር።
11
ከፀሐይ መውጫ ጀምሮ እስከ መግቢያዋ ድረስ ስሜ በአሕዛብ ዘንድ ታላቅ ይሆናልና፤ በየስፍራውም ለስሜ ዕጣን ያጥናሉ፥ ንጹሕም ቍርባን ያቀርባሉ፤ ስሜ በአሕዛብ ዘንድ ታላቅ ይሆናልና፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር።
12
እናንተ ግን። የእግዚአብሔር ገበታ ርኩስ ነው፤ ፍሬውና መብሉም የተናቀ ነው በማለታችሁ አስነቀፋችሁት።
13
እናንተ። እነሆ፥ ይህ ድካም ነው ብላችሁ ጢቅ አላችሁበት፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር፤ በቅሚያ የያዛችሁትንም አንካሳውንም የታመመውንም አቅርባችኋል፤ እንዲሁ ቍርባንን ታመጣላችሁ፤ በውኑ ከእጃችሁ ይህን ልቀበለውን? ይላል እግዚአብሔር።
14
እኔ ታላቅ ንጉሥ ነኝና፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር፥ ስሜም በአሕዛብ ዘንድ የተፈራ ነውና በመንጋው ውስጥ ተባት እያለው ለጌታ ተስሎ ነውረኛውን የሚሠዋ ሸንጋይ ሰው ርጉም ይሁን።

1
An oracle: the word of Yahweh to Israel by Malachi.
2
"I have loved you," says Yahweh. Yet you say, "How have you loved us?" "Wasn''t Esau Jacob''s brother?" says Yahweh, "Yet I loved Jacob;
3
but Esau I hated, and made his mountains a desolation, and gave his heritage to the jackals of the wilderness."
4
Whereas Edom says, "We are beaten down, but we will return and build the waste places;" thus says Yahweh of Armies, "They shall build, but I will throw down; and men will call them ''The Wicked Land,'' even the people against whom Yahweh shows wrath forever."
5
Your eyes will see, and you will say, "Yahweh is great-- even beyond the border of Israel!"
6
"A son honors his father, and a servant his master. If I am a father, then where is my honor? And if I am a master, where is the respect due me? Says Yahweh of Armies to you, priests, who despise my name. You say, ''How have we despised your name?''
7
You offer polluted bread on my altar. You say, ''How have we polluted you?'' In that you say, ''Yahweh''s table contemptible.''
8
When you offer the blind for sacrifice, isn''t that evil? And when you offer the lame and sick, isn''t that evil? Present it now to your governor! Will he be pleased with you? Or will he accept your person?" says Yahweh of Armies.
9
"Now, please entreat the favor of God, that he may be gracious to us. With this, will he accept any of you?" says Yahweh of Armies.
10
"Oh that there were one among you who would shut the doors, that you might not kindle fire on my altar in vain! I have no pleasure in you," says Yahweh of Armies, "neither will I accept an offering at your hand.
11
For from the rising of the sun even to the going down of the same, my name is great among the nations, and in every place incense will be offered to my name, and a pure offering: for my name is great among the nations," says Yahweh of Armies.
12
"But you profane it, in that you say, ''Yahweh''s table is polluted, and its fruit, even its food, is contemptible.''
13
You say also, ''Behold, what a weariness it is!'' and you have sniffed at it," says Yahweh of Armies; "and you have brought that which was taken by violence, the lame, and the sick; thus you bring the offering. Should I accept this at your hand?" says Yahweh.
14
"But the deceiver is cursed, who has in his flock a male, and vows, and sacrifices to the Lord a blemished thing; for I am a great King," says Yahweh of Armies, "and my name is awesome among the nations."