1-4
የከበርህ ቴዎፍሎስ ሆይ፥ ከመጀመሪያው በዓይን ያዩትና የቃሉ አገልጋዮች የሆኑት እንዳስተላለፉልን፥ በኛ ዘንድ ስለ ተፈጸመው ነገር ብዙዎች ታሪክን በየተራው ለማዘጋጀት ስለ ሞከሩ፥ እኔ ደግሞ ስለ ተማርኸው ቃል እርግጡን እንድታውቅ በጥንቃቄ ሁሉን ከመጀመሪያው ተከትዬ በየተራው ልጽፍልህ መልካም ሆኖ ታየኝ።
5
በይሁዳ ንጉሥ በሄሮድስ ዘመን ከአብያ ክፍል የሆነ ዘካርያስ የሚባል አንድ ካህን ነበረ፤ ሚስቱም ከአሮን ልጆች ነበረች፥ ስምዋም ኤልሳቤጥ ነበረ።
6
ሁለቱም በጌታ ትእዛዝና ሕግጋት ሁሉ ያለ ነቀፋ እየሄዱ በእግዚአብሔር ፊት ጻድቃን ነበሩ።
7
ኤልሳቤጥም መካን ነበረችና ልጅ አልነበራቸውም፤ ሁለቱም በዕድሜያቸው አርጅተው ነበር።
8
እርሱም በክፍሉ ተራ በእግዚአብሔር ፊት ሲያገለግል፥
9
እንደ ካህናት ሥርዓት ወደ ጌታ ቤተ መቅደስ ገብቶ ለማጠን ዕጣ ደረሰበት።
10
በዕጣንም ጊዜ ሕዝቡ ሁሉ በውጭ ቆመው ይጸልዩ ነበር።
11
የጌታም መልአክ በዕጣኑ መሠዊያ ቀኝ ቆሞ ታየው።
12
ዘካርያስም ባየው ጊዜ ደነገጠ፥ ፍርሃትም ወደቀበት።
13
መልአኩም እንዲህ አለው። ዘካርያስ ሆይ፥ ጸሎትህ ተሰምቶልሃልና አትፍራ ሚስትህ ኤልሳቤጥም ወንድ ልጅ ትወልድልሃለች፥ ስሙንም ዮሐንስ ትለዋለህ።
14
ደስታና ተድላም ይሆንልሃል፥ በመወለዱም ብዙዎች ደስ ይላቸዋል።
15
በጌታ ፊት ታላቅ ይሆናልና፥ የወይን ጠጅና የሚያሰክር መጠጥ አይጠጣም፤ ገናም በእናቱ ማኅፀን ሳለ መንፈስ ቅዱስ ይሞላበታል፤
16
ከእስራኤልም ልጆች ብዙዎችን ወደ ጌታ ወደ አምላካቸው ይመልሳል።
17
እርሱም የተዘጋጁትን ሕዝብ ለጌታ እንዲያሰናዳ፥ የአባቶችን ልብ ወደ ልጆች የማይታዘዙትንም ወደ ጻድቃን ጥበብ ይመልስ ዘንድ በኤልያስ መንፈስና ኃይል በፊቱ ይሄዳል።
18
ዘካርያስም መልአኩን። እኔ ሽማግሌ ነኝ ምስቴም በዕድሜዋ አርጅታለችና ይህን በምን አውቃለሁ? አለው።
19
መልአኩም መልሶ። እኔ በእግዚአብሔር ፊት የምቆመው ገብርኤል ነኝ፥ እንድናገርህም ይህችንም የምሥራች እንድሰብክልህ ተልኬ ነበር፤
20
እነሆም፥ በጊዜው የሚፈጸመውን ቃሌን ስላላመንህ፥ ይህ ነገር እስከሚሆን ቀን ድረስ ዲዳ ትሆናለህ መናገርም አትችልም አለው።
21
ሕዝቡም ዘካርያስን ይጠብቁት ነበር፤ በቤተ መቅደስም ውስጥ ስለ ዘገየ ይደነቁ ነበር።
22
በወጣም ጊዜ ሊነግራቸው አልቻለም፥ በቤተ መቅደስም ራእይ እንዳየ አስተዋሉ፤ እርሱም ይጠቅሳቸው ነበር፤ ድዳም ሆኖ ኖረ።
23
የማገልገሉም ወራት ሲፈጸም ወደ ቤቱ ሄደ።
24-25
ከዚህም ወራት በኋላ ሚስቱ ኤልሳቤጥ ፀነሰችና። ነቀፌታዬን ከሰው መካከል ያስወግድልኝ ዘንድ ጌታ በተመለከተበት ወራት እንዲህ አድርጎልኛል ስትል ራስዋን አምስት ወር ሰወረች።
26
በስድስተኛውም ወር መልአኩ ገብርኤል ናዝሬት ወደምትባል ወደ ገሊላ ከተማ፥
27
ከዳዊት ወገን ለሆነው ዮሴፍ ለሚባል ሰው ወደ ታጨች ወደ አንዲት ድንግል ከእግዚአብሔር ዘንድ ተላከ፥ የድንግሊቱም ስም ማርያም ነበረ።
28
መልአኩም ወደ እርስዋ ገብቶ። ደስ ይበልሽ፥ ጸጋ የሞላብሽ ሆይ፥ ጌታ ከአንቺ ጋር ነው፤ አንቺ ከሴቶች መካከል የተባረክሽ ነሽ አላት።
29
እርስዋም ባየችው ጊዜ ከንግግሩ በጣም ደነገጠችና። ይህ እንዴት ያለ ሰላምታ ነው? ብላ አሰበች።
30
መልአኩም እንዲህ አላት። ማርያም ሆይ፥ በእግዚአብሔር ፊት ጸጋ አግኝተሻልና አትፍሪ።
31
እነሆም፥ ትፀንሻለሽ ወንድ ልጅም ትወልጃለሽ፥ ስሙንም ኢየሱስ ትዪዋለሽ።
32
እርሱ ታላቅ ይሆናል የልዑል ልጅም ይባላል፥ ጌታ አምላክም የአባቱን የዳዊትን ዙፋን ይሰጠዋል፤
33
በያዕቆብ ቤትም ላይ ለዘለላም ይነግሣል፥ ለመንግሥቱም መጨረሻ የለውም።
34
ማርያምም መልአኩን። ወንድ ስለማላውቅ ይህ እንዴት ይሆናል? አለችው።
35
መልአኩም መልሶ እንዲህ አላት። መንፈስ ቅዱስ በአንቺ ላይ ይመጣል፥ የልዑልም ኃይል ይጸልልሻል ስለዚህ ደግሞ ከአንቺ የሚወለደው ቅዱስ የእግዚአብሔር ልጅ ይባላል።
36
እነሆም ዘመድሽ ኤልሳቤጥ፥ እርስዋ ደግሞ በእርጅናዋ ወንድ ልጅ ፀንሳለች፥ ለእርስዋም መካን ትባል ለነበረችው ይህ ስድስተኛ ወር ነው፤
37
ለእግዚአብሔር የሚሳነው ነገር የለምና።
38
ማርያምም። እነሆኝ የጌታ ባሪያ እንደ ቃልህ ይሁንልኝ አለች። መልአኩም ከእርስዋ ሄደ።
39
ማርያምም በዚያ ወራት ተነሥታ ወደ ተራራማው አገር ወደ ይሁዳ ከተማ ፈጥና ወጣች፥
40
ወደ ዘካርያስም ቤት ገብታ ኤልሳቤጥን ተሳለመቻት።
41
ኤልሳቤጥም የማርያምን ሰላምታ በሰማች ጊዜ ፅንሱ በማኅፀንዋ ውስጥ ዘለለ፤ በኤልሳቤጥም መንፈስ ቅዱስ ሞላባት፥
42
በታላቅ ድምፅም ጮኻ እንዲህ አለች። አንቺ ከሴቶች መካከል የተባረክሽ ነሽ፥ የማኅፀንሽም ፍሬ የተባረከ ነው።
43
የጌታዬ እናት ወደ እኔ ትመጣ ዘንድ እንዴት ይሆንልኛል?
44
እነሆ፥ የሰላምታሽ ድምጽ በጆሮዬ በመጣ ጊዜ ፅንሱ በማኅፀኔ በደስታ ዘሎአልና።
45
ከጌታ፤ የተነገረላት ቃል ይፈጸማልና ያመነች ብፅዕት ናት።
46
ማርያምም እንዲህ አለች።
47
ነፍሴ ጌታን ታከብረዋለች፥ መንፈሴም በአምላኬ በመድኃኒቴ ሐሴት ታደርጋለች፤
48
የባሪያይቱን ውርደት ተመልክቶአልና። እነሆም፥ ከዛሬ ጀምሮ ትውልድ ሁሉ ብፅዕት ይሉኛል፤
49
ብርቱ የሆነ እርሱ በእኔ ታላቅ ሥራ አድርጎአልና፤ ስሙም ቅዱስ ነው።
50
ምሕረቱም ለሚፈሩት እስከ ትውልድና ትውልድ ይኖራል።
51
በክንዱ ኃይል አድርጎአል፤ ትዕቢተኞችን በልባቸው አሳብ በትኖአል፤
52
ገዥዎችን ከዙፋናቸው አዋርዶአል፤ ትሑታንንም ከፍ አድርጎአል፤
53
የተራቡትን በበጎ ነገር አጥግቦአል፤ ባለ ጠጎችንም ባዶአቸውን ሰዶአቸዋል።
54-55
ለአባቶቻችን እንደ ተናገረ፥ ለአብርሃምና ለዘሩ ለዘላለም ምሕረቱ ትዝ እያለው እስራኤልን ብላቴናውን ረድቶአል።
56
ማርያምም ሦስት ወር የሚያህል በእርስዋ ዘንድ ተቀመጠች ወደ ቤትዋም ተመለሰች።
57
የኤልሳቤጥም የመውለጃዋ ጊዜ ደረሰ፥ ወንድ ልጅም ወለደች።
58
ጎረቤቶችዋም ዘመዶችዋም ጌታ ምሕረቱን እንዳገነነላት ሰምተው ከእርስዋ ጋር ደስ አላቸው።
59
በስምንተኛውም ቀን ሕፃኑን ሊገርዙት መጡ፥ በአባቱም ስም ዘካርያስ ሊሉት ወደዱ።
60
እናቱ ግን መልሳ። አይሆንም፥ ዮሐንስ ይባል እንጂ አለች።
61
እነርሱም። ከወገንሽ ማንም በዚህ ስም የተጠራ የለም አሉአት።
62
አባቱንም ማን ሊባል እንዲወድ ጠቀሱት።
63
ብራናም ለምኖ። ስሙ ዮሐንስ ነው ብሎ ጻፈ። ሁሉም አደነቁ።
64
ያንጊዜም አፉ ተከፈተ መላሱም ተፈታ እግዚአብሔርንም እየባረከ ተናገረ።
65
ለጎረቤቶቻቸውም ሁሉ ፍርሃት ሆነ፤ ይህም ሁሉ ነገር በይሁዳ በተራራማው አገር ሁሉ ተወራ፤
66
የሰሙትም ሁሉ። እንኪያ ይህ ሕፃን ምን ይሆን? እያሉ በልባቸው አኖሩት፤ የጌታ እጅ ከእርሱ ጋር ነበረችና።
67
አባቱ ዘካርያስም መንፈስ ቅዱስ ሞላበትና ትንቢት ተናገረ እንዲህም አለ።
68
የእስራኤል ጌታ አምላክ ይባረክ፥ ጐብኝቶ ለሕዝቡ ቤዛ አድርጎአልና፤
69-70
ከጥንት ጀምሮ በነበሩት በቅዱሳን ነቢያት አፍ እንደ ተናገረ፥ በብላቴናው በዳዊት ቤት የመዳን ቀንድን አስነስቶልናል፤
71
ማዳኑም ከወደረኞቻችንና ከሚጠሉን ሁሉ እጅ ነው፤
72-73
እንደዚህ ለአባቶቻችን ምሕረት አደረገ፤ ለአባታችን ለአብርሃምም የማለውን መሐላውን ቅዱሱን ኪዳን አሰበ፤
74-75
በእርሱም ከጠላቶቻችን እጅ ድነን በዘመናችን ሁሉ ያለ ፍርሃት በቅድስናና በጽድቅ በፊቱ እንድናገለግለው ሰጠን።
76
ደግሞም አንተ ሕፃን ሆይ፥ የልዑል ነቢይ ትባላለህ፥ መንገዱን ልትጠርግ በጌታ ፊት ትሄዳለህና፤
77
እንደዚህም የኃጢአታቸው ስርየት የሆነውን የመዳን እውቀት ለሕዝቡ ትሰጣለህ፤
78
ይህም ከላይ የመጣ ብርሃን በጐበኘበት በአምላካችን ምሕረትና ርኅራኄ ምክንያት ነው፤
79
ብርሃኑም በጨለማና በሞት ጥላ ተቀምጠው ላሉት ያበራል እግሮቻችንንም በሰላም መንገድ ያቀናል።
80
ሕፃኑም አደገ በመንፈስም ጠነከረ፥ ለእስራኤልም እስከ ታየበት ቀን ድረስ በምድረ በዳ ኖረ።

1
Since many have undertaken to set in order a narrative concerning those matters which have been fulfilled among us,
2
even as those who from the beginning were eyewitnesses and servants of the word delivered them to us,
3
it seemed good to me also, having traced the course of all things accurately from the first, to write to you in order, most excellent Theophilus;
4
that you might know the certainty concerning the things in which you were instructed.
5
There was in the days of Herod, the king of Judea, a certain priest named Zacharias, of the priestly division of Abijah. He had a wife of the daughters of Aaron, and her name was Elizabeth.
6
They were both righteous before God, walking blamelessly in all the commandments and ordinances of the Lord.
7
But they had no child, because Elizabeth was barren, and they both were well advanced in years.
8
Now it happened, while he executed the priest''s office before God in the order of his division,
9
according to the custom of the priest''s office, his lot was to enter into the temple of the Lord and burn incense.
10
The whole multitude of the people were praying outside at the hour of incense.
11
An angel of the Lord appeared to him, standing on the right side of the altar of incense.
12
Zacharias was troubled when he saw him, and fear fell upon him.
13
But the angel said to him, "Don''t be afraid, Zacharias, because your request has been heard, and your wife, Elizabeth, will bear you a son, and you shall call his name John.
14
You will have joy and gladness; and many will rejoice at his birth.
15
For he will be great in the sight of the Lord, and he will drink no wine nor strong drink. He will be filled with the Holy Spirit, even from his mother''s womb.
16
He will turn many of the children of Israel to the Lord, their God.
17
He will go before him in the spirit and power of Elijah, ''to turn the hearts of the fathers to the children,'' and the disobedient to the wisdom of the just; to make ready a people prepared for the Lord."
18
Zacharias said to the angel, "How can I be sure of this? For I am an old man, and my wife is well advanced in years."
19
The angel answered him, "I am Gabriel, who stands in the presence of God. I was sent to speak to you, and to bring you this good news.
20
Behold, you will be silent and not able to speak, until the day that these things will happen, because you didn''t believe my words, which will be fulfilled in their proper time."
21
The people were waiting for Zacharias, and they marveled that he delayed in the temple.
22
When he came out, he could not speak to them, and they perceived that he had seen a vision in the temple. He continued making signs to them, and remained mute.
23
It happened, when the days of his service were fulfilled, he departed to his house.
24
After these days Elizabeth, his wife, conceived, and she hid herself five months, saying,
25
"Thus has the Lord done to me in the days in which he looked at me, to take away my reproach among men."
26
Now in the sixth month, the angel Gabriel was sent from God to a city of Galilee, named Nazareth,
27
to a virgin pledged to be married to a man whose name was Joseph, of the house of David. The virgin''s name was Mary.
28
Having come in, the angel said to her, "Rejoice, you highly favored one! The Lord is with you. Blessed are you among women!"
29
But when she saw him, she was greatly troubled at the saying, and considered what kind of salutation this might be.
30
The angel said to her, "Don''t be afraid, Mary, for you have found favor with God.
31
Behold, you will conceive in your womb, and bring forth a son, and will call his name ''Jesus.''
32
He will be great, and will be called the Son of the Most High. The Lord God will give him the throne of his father, David,
33
and he will reign over the house of Jacob forever. There will be no end to his Kingdom."
34
Mary said to the angel, "How can this be, seeing I am a virgin?"
35
The angel answered her, "The Holy Spirit will come on you, and the power of the Most High will overshadow you. Therefore also the holy one who is born from you will be called the Son of God.
36
Behold, Elizabeth, your relative, also has conceived a son in her old age; and this is the sixth month with her who was called barren.
37
For everything spoken by God is possible."
38
Mary said, "Behold, the handmaid of the Lord; be it to me according to your word." The angel departed from her.
39
Mary arose in those days and went into the hill country with haste, into a city of Judah,
40
and entered into the house of Zacharias and greeted Elizabeth.
41
It happened, when Elizabeth heard Mary''s greeting, that the baby leaped in her womb, and Elizabeth was filled with the Holy Spirit.
42
She called out with a loud voice, and said, "Blessed are you among women, and blessed is the fruit of your womb!
43
Why am I so favored, that the mother of my Lord should come to me?
44
For behold, when the voice of your greeting came into my ears, the baby leaped in my womb for joy!
45
Blessed is she who believed, for there will be a fulfillment of the things which have been spoken to her from the Lord!"
46
Mary said, "My soul magnifies the Lord.
47
My spirit has rejoiced in God my Savior,
48
for he has looked at the humble state of his handmaid. For behold, from now on, all generations will call me blessed.
49
For he who is mighty has done great things for me. Holy is his name.
50
His mercy is for generations of generations on those who fear him.
51
He has shown strength with his arm. He has scattered the proud in the imagination of their heart.
52
He has put down princes from their thrones. And has exalted the lowly.
53
He has filled the hungry with good things. He has sent the rich away empty.
54
He has given help to Israel, his servant, that he might remember mercy,
55
As he spoke to our fathers, to Abraham and his seed forever."
56
Mary stayed with her about three months, and then returned to her house.
57
Now the time that Elizabeth should give birth was fulfilled, and she brought forth a son.
58
Her neighbors and her relatives heard that the Lord had magnified his mercy towards her, and they rejoiced with her.
59
It happened on the eighth day, that they came to circumcise the child; and they would have called him Zacharias, after the name of the father.
60
His mother answered, "Not so; but he will be called John."
61
They said to her, "There is no one among your relatives who is called by this name."
62
They made signs to his father, what he would have him called.
63
He asked for a writing tablet, and wrote, "His name is John." They all marveled.
64
His mouth was opened immediately, and his tongue freed, and he spoke, blessing God.
65
Fear came on all who lived around them, and all these sayings were talked about throughout all the hill country of Judea.
66
All who heard them laid them up in their heart, saying, "What then will this child be?" The hand of the Lord was with him.
67
His father, Zacharias, was filled with the Holy Spirit, and prophesied, saying,
68
"Blessed be the Lord, the God of Israel, for he has visited and worked redemption for his people;
69
and has raised up a horn of salvation for us in the house of his servant David
70
(as he spoke by the mouth of his holy prophets who have been from of old),
71
salvation from our enemies, and from the hand of all who hate us;
72
to show mercy towards our fathers, to remember his holy covenant,
73
the oath which he spoke to Abraham, our father,
74
to grant to us that we, being delivered out of the hand of our enemies, should serve him without fear,
75
In holiness and righteousness before him all the days of our life.
76
And you, child, will be called a prophet of the Most High, for you will go before the face of the Lord to make ready his ways,
77
to give knowledge of salvation to his people by the remission of their sins,
78
because of the tender mercy of our God, whereby the dawn from on high will visit us,
79
to shine on those who sit in darkness and the shadow of death; to guide our feet into the way of peace."
80
The child was growing, and becoming strong in spirit, and was in the desert until the day of his public appearance to Israel.